ማርሐሺ
ማርሐሺ (ባርሐሺ፣ ዋራሕሼ) በጥንት በኤላም አጠገብ የተገኘ አገር ነበር። በአዳብ ንጉሥ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ ግዛት ከ፯ቱ ክፍላገራት ከኤላምና ጉቲዩም መካከል በአንድ መዝገብ ቢቆጠርም፣ ከእላም ምሥራቅ በጂሮፍት አካባቢ እንደ ነበር ይታሥባል። ደግሞ የማርሐሺ አለቃ ሚጊር-ኤንሊል በአመጽ ተነሥቶ ሉጋል-አኔ-ሙንዱ እንደ ተወጋው ይላል።
በኋላ የአካድ ንጉሥ ታላቁ ሳርጎን ማሐሺን ያዘ። ሆኖም በሳርጎን ልጅ በሪሙሽ ላይ የማርሐሺ ገዢ አባልጋማሽና ሻለቃው ሲድጋው ከአዋን ገዥ ኤማህሲኒ ጋር እንደገና በአመጽ ተነሥተው ተሸነፉ። የሪሙሽም ተከታይ ናራም-ሲን ደግሞ ማርሐሲን ድል አደረገ።
ከዚህም በኋላ በኡር መንግሥት ዘመን የኡር ንጉሥ ሹልጊ በ18ኛው ዓመት ሴት ልጁን ኒያሊሚዳሹን ለማርሐሺ ንጉሥ ሊባኑክሻባሽ በጋብቻ ስምምነት ሰጣት። ይሁንና ይህ ሰላም አጭር ነበር፤ የሹልጊ ተከታይ አማር-ሲን በማርሐሺ አዲስ ንጉሥ በአርዊሉክፒ ላይ እንደ ዘመተ ይመዝገባልና።
የባቢሎን ንጉሥ ሐሙራቢ ፴ኛው የዓመት ስም ሐሙራቢ የኤላምን ሠራዊት እንዲሁም ከማርሐሺ፣ ሱባርቱ፣ ጉቲዩም፣ ቱፕሊያሽ (ኤሽኑና) እና ከማጊዩም ጠረፎች የተሰበሰበውን ብዛት በዘመቻ ያሸነፈበት ዓመት ይባል ነበር።
🔥 Top keywords: ዋናው ገጽልዩ:Searchአፈወርቅ ተክሌሥርዓተ ነጥቦችኤችአይቪዓፄ ቴዎድሮስቅዱስ ያሬድየአድዋ ጦርነትአበበ ቢቂላኢትዮጵያዳግማዊ ምኒልክ2ኛው ዓለማዊ ጦርነትላሊበላገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችየአክሱም ሐውልትጉራጌልዩ:RecentChangesገበጣአክሱምየጋብቻ ሥነ-ስርዓትቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴጥላሁን ገሠሠደራርቱ ቱሉኤድስጸጋዬ ገብረ መድህንሀዲስ ዓለማየሁአለቃ ገብረ ሐናአማርኛአዲስ አበባውክፔዲያእርዳታ:ይዞታውክፔዲያ ውይይት:ምንጭጌስዕል:Keristo1.pdfመሬትአርሰናል የእግር ኳስ ክለብማንችስተር ዩናይትድበዓሉ ግርማመዝገበ ቃላትገብረ ክርስቶስ ደስታ