ሩማን

(ከሮማን የተዛወረ)

ሩማን ወይም ሮማን (ሮማይስጥ፦ Punica granatum) ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሁም በዓለም የሚገኝ ተክል ነው።

ሩማን

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

በሩማን ወገን ውስጥ አንድ ሌላ ዝርያ ብቻ አለ፤ እሱም የሱቁጥራ ሩማን (P. protopunica) ሲሆን መገኛው የየመን ደሴት ሱቁጥራ ነው።

በብዙ አገራት ይታረሳል፣ በብዛት በእስያ፣ በሕንድ ይታረሳል። በሕንድ ባሕል መድሃኒት («አዩርቬዳ») ደግሞ ይጠቀማል።

አስተዳደግ

በኢትዮጵያ ብዙ ጊዜ የማይታረስ፣ በአንዳንድ አጥር ግቢ ይገኛል።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

የተክሉ ጥቅም

ፍሬው ቁርጥ አርጎ የሚስብ ነው፣ ለተቅማጥና ለተመሳሳይ ይበላል።

ቅጠሉ ትልን ለመግደል ይጠቀማል፣ አንዳንዴም እንደ ሰላጣ ይበላል።

ቅርንጫፎቹ የወለል መጥረጊያ ለመሥራት ያገልግላሉ።[1]