ሶፊያ ሮታሩ

ሶፊያ ሮታሩ (ሞልዶቭኛ፦ Sofia Mihailovna Rotaru-Evdokimenko /ሶፊያ ሚሃይሎቭና ሮታሩ-ኤቭዶኪመንኮ/ ፤ ዩክራይንኛ፦ Софія Ротару) ሩሳዊትኡክራይናዊትሞልዶቫዊት እና ቀድሞ ሶቭየት ዘፋኝ፣ ሙዚቀኛ፣ ጭፍረኛ፣ ተዋናይና ደራሲ ነች። ስለ ድምጿና በምሥራቅ አውሮፓ በተለይ ትታወቃለች።

በዜና ማሰራጫ በኩል «የዘመናዊ ሙዚቃ ንግሥት» ተብላ ተሰይማለች[1]። በ1986 እ.ኤ.አ. ስመ ጥሩ ማእረግ «የሶቭየት ህብረት ሕዝብ ዛፋኝ» የተቀበለች መጀመርያ ዘመናዊ ሴት ዘፋኝ ሆነች፤ በ2000 እ.ኤ.አ. ደግሞ የ20ኛው ክለ ዘመን ዘፋኝ ተባለች።

ዛሬ ሶፊያ ሮታሩ የዩክሬን ዜጋ ሆና በክሪሜያና በያልታ ክብር ኗሪ ነች። ዋና መኖርያዋ ያልታ ሲሆን ደግሞ ቤቶች በመስኮብክዬቭና ባደን-ባደን አሏት። በርካታ ከፈትኛ ሽልማቶችም አሏት፤ ከነዚህም መካከል የዩክሬን ሶቭዬት ሪፐብሊክ ክብር ዘፋኝ፣ የዩክሬን ሕዝብ ዘፋኝ፣ የሞልዳቪያ ሶቭዬት ሪበብሊክ ሕዝብ ዘፋኝ፣ ወዘተ ናቸው።

www.sofiarotaru.com