ቆፍ

ቀ ቁ ቂ ቃ ቄ ቅ ቆ ቋ ቈ ቊ



አቡጊዳ ታሪክ

ቆፍ (ወይም ቃፍ) በጥንታዊ አቡጊዳ ተራ 19ኛው ፊደል ነው። እንዲሁም በከነዓንአራማያዕብራይስጥ ፊደሎች በሶርያም 19ኛው ፊደል "ቆፍ" ይባላል። በዓረብኛ ደግሞ ተመሳሳይ ፊደል "ቃፍ" ተብሎ በ"አብጃድ" ተራ 19ኛ ነው።

ታሪክ

ተመሳሳይ ግብፃዊ ስዕልቅድመ-ሴማዊሣባግዕዝ
V24


የቆፍ መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ አመልማሎ (የሸማኔ ዕቃ) ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። አጠራሩ ግን "ወጅ" ነበር። በግብፅ የሠሩት ሴማውያን ግን በቋንቋቸው "ቆፍ" ስላሉት፣ ይህ ስዕል "ቀ" ሆኖ እንዲሰማ መጣ።

ከነዓንአራማያ ዕብራይስጥሶርያዓረብኛ
ק ق


የከነዓን "ቆፍ" እንዲሁም ከዚህ ምልክት ተወስዶ በዚያ መንገድ የዕብራይስጥና የአራማያ "ቆፍ" የአረብኛም "ቃፍ" ወለደ። ከዚህ በላይ የድሮ የግሪክ አልፋቤት ፊደል "ቆፓ" ( ) አባት ሆነ። እሱም የላቲን አልፋቤት (Q q) ወላጅ ሆነ። ስለዚህ እነዚህ ሁሉ የ"ቆፍ" ሩቅ ዘመዶች ሊባሉ ይቻላል። በተጨማሪ የግዕዝ ቁጥር (ዘጠና) ከግሪኩ በመወሰዱ እሱም የ"ቀ" ዘመድ ነው።