ኢ-ገዳይ መሣርያዎች

ኢ-ገዳይ መሣርያዎች በብዙ የሠለጠኑ አገራት የሕዝብን ተቃውሞ ለማስተዳደር የሚጠቅመው ዘዴ ነው። በሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፖሊሶች ወይም ወታደሮች ታላቅ የሕዝብ እልቂጥ ባለመፈልጋቸው፣ በዚያው ፈንታ «ኢ-ገዳይ መሣርያ» አላቸው። ለምሳሌ፦

  • የውሃ መድፍ
  • ዕምባ አውጭ ጋዝ
  • የጎማ ጥይት
  • ቴዘር (ኤሌክትሪክ ድንጋጤ የሚያቀርብ በትር)

እነዚህ መሣርያዎች ሠልፈኞች ወይም ዜጎች እንዳይገደሉ ስለሚታሥቡ ብዙዎች ጊዘዎች በዘመናዊ ዓለም ይመረጣሉ።