እንዳሁላ

እንዳሁላእንዳሆህላእንዶሃህላ (Kalanchoe) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ወገን ነው።

አንድ የእንዳሁላ አይነት ዝርያ

እነዚህ የእንዳሁላ አይነቶች ናቸው፦

  • አንጩራ K. petitiana
  • ሽልቀቅ ?
  • የቆላ እንዳሁላ K. deficiens

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

እንዳሁላ ውሀማ የተባሉ ተክሎች ናቸው። የተላያዩ ዝርያዎች አበቦችም ልዩ ልዩ መልኮች አላቸው።

አስተዳደግ

K. pinnata፦ ይህ ዝርያ በእፃዊ ተዋልዶ በጫፉ ላይ ሕጻናት ይወልዳል።

ብዙ ውሃ አይፈልጉም፣ በቀላሉ ይስፋፋል።

አንዱ ዝርያ K. pinnata በእፃዊ ተዋልዶ ብቻ ራሱን ያበዛል።

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

ከአለሙ 125 የእንዳሁላ ዝርያዎች፣ 60 ዝርያዎች በዱር ከማዳጋስካር ናቸው፣ 56 ዝርያዎች ከደቡባዊ ወይም ምሥራቅ አፍሪካ ናቸው፤ አንድ ዝርያ ብቻ ከአሜሪካዎች ነው።

ብዙ አይነቶች በኢትዮጵያ አሉ፣ አንዳንድ በደረቅ ድንጋያማ፣ ለሎችም በፈሳሽ ዳር ወይም በጫካ ዳር ይበቅላሉ።

የተክሉ ጥቅም

በዋናነት ለቤት ማገጫ ይታደጋል።

በኢትዮጵያ ባህላዊ መድሃኒት፣ የእንዳሁላ ቅጠሎች ለቁስል፣ ለብጉንጅ፣ ለእባጭ፣ ለቆዳ ችግሮች ለማከም ተጠቅመዋል። እንዲሁም የበሬ ቀንበር ቁስል ለማከም ተጠቅመዋል።

ትኩስ ሥሮቹ ለጨብጡ፣ ለሆድ ትል ሕክምና ተጠቅመዋል። ይህ ሥር እንደ ሻይ ይጠመቃል፣ በጣም ሃይለኛ ሲሆን ጉዳት እንዳያደርግ በአነስተኛ መጠን ብቻ ይጠጣል።[1]

በሌላ ጥናቶች ዘንድ፣ የK. petitiana (የአንጩራ) አገዳ መረቅ ለኪንታሮት፣ የቅጠሉም ጭማቂ በቅቤ ለጥፍ ለተሰበረ አጥንት ያክማል።[2] ወይም ለማበጥ፣ ሥሩ በቀጥታ ማስገባት ይደረጋል።[3]

ብዙ ዝርያዎች፣ በተለይ ለከብት፣ ለልብ መርዛም ናቸው።[4][5]

በሌሎች አገራት በህላዊ ሕክምናዎች፣ ለቁርጥማት፣ ለማበጥ፣ ለልክፈቶች ተጠቅመዋል። በትሪኒዳድ ባህላዊ ሕክምና፣ K. pinnata ለደም ግፊት እንዲሰጥ ይዘገባል።[6]