ዳካር

ዳካር (Dakar) የሴኔጋል ዋና ከተማ ነው።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር 2,476,400 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 14°38′ ሰሜን ኬክሮስ እና 17°27′ ምዕራብ ኬንትሮስ በካፕ-ቨርት ልሳነ ምድር ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

ታሪክ

በ1422 ዓ.ም. በስሜን ዳካር ዮፍ ከተማ ላየነ በተባለ ሱፊ እስላም ክፍልፋይ ተመሠረተ። በ1436 ዓ.ም. ደግሞ ፖርቱጊዝ በጎሬ ደሴት ላይ ደርሰው ሰፈሩበትና ከ1528 ዓ.ም. ጀምሮ የባርያ ፍንገላ ማእከል ሆነ። በዚሁ ጊዜ ልሳነ ምድሩ በጆሎፍ (ዎሎፍ) መንግሥት ሥልጣን ነበረ። የጆሎፍ ምዕራብ አውራጃ ካዮር ግን ከነልሳነ ምድሩ በ1541 ዓ.ም. ተገንጥሎ የራሱ መንግሥት ሆነ።