2 ነቢሪራው

==

2 ነቢሪራው ?
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት1613 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ1 ነቢሪራው
ተከታይሰመንሬ
ሥርወ-መንግሥት16ኛው ሥርወ መንግሥት

==


2 ነቢሪራው ምናልባት በላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (16ኛው ሥርወ መንግሥት) በ1614 ዓክልበ. ያሕል የገዛ ፈርዖን ነበረ።

ታሪካዊ ሕሊናው ምንም አልተረጋገጠም። ስሙ የሚገኝ በቶሪኖ ቀኖና ዝርዝር ብቻ ነው። ከ1 ነቢሪራው ወይም «ነቢራውሬ» ቀጥሎ ሁለተኛው «ነቢራውሬ» ወይም «ነቢታውሬ» አለው። ስለዚህ ለአጭር ጊዜ ከነገሡት ፈርዖኖች መካከል እንደ ሆነ ይገመታል።

በተጨማሪ ከዚያ 1500 ዓመት በኋላ በ150 ዓክልበ. ያህል የተሠራ አንድ ጣኦት ምስል ይታወቃል፤ በመሠረቱ በየጎኑ «ያለፉት ፈርዖን ሰዋጀንሬ»፣ «ያለፉት ፈርዖን ነፈርካሬ»፣ «አህሞስ»ና «ቢንፑ» ይጠቀሳል። በአንድ መላ ምት፣ ከጥንታዊ ምስል ተቀድቶ ፈርዖን ነቢሪራው ሰዋጀንሬ፣ ልጁም 2 ነቢሪራው ነፈርካሬ፣ እና በዘመኑ የኖሩት ልዑላን መስፍኖች አህሞስና ቢንፑ ይጠቀሳሉ። በዚህ አስተሳሰብ «ነፈርካሬ» ሲል የዚህ 2 ነቢሪራው ሌላ ስም ሊሆን ይችላል። ሆኖም የ2 ነቢሪራው ስም በቶሪኖ ቀኖና ብቻ ስለሚገኝ ሌላ ስሙ አይታወቅለትም።

ቀዳሚው
1 ነቢሪራው
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1613 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሰመንሬ