==
ሰኸምካሬ ሶንበፍ | |
---|---|
ስሙ «ንጉሥ ሰኸምካሬ የንጉሥ አመነምሃት ልጅ» የተጻፈበት ምስል | |
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1816-1812 ዓክልበ. |
ቀዳሚ | ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ |
ተከታይ | ነሪካሬ |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
አባት | 4 አመነምሃት? |
==
ሰኸምካሬ ሶንበፍ ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1816 እስከ 1812 ዓክልበ. ግድም ድረስ የገዛ ፈርዖን ነበረ። የወንድሙ ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ ተከታይ ነበረ።
በግብጽ ታሪክ ሊቅ ኪም ራይሆልት አስተሳሰብ፣ ይህ ፈርዖን የ4 አመነምሃት ልጅና የ፩ ሶበክሆተፕ ወንድም ነበር። ሌሎች መምህሮች ግን ከተከታዩ ከሰኸምካሬ 5 አመነምሃት ጋር አንድ አድርገውታል። ራይሆልት እንደሚያስረዳው፣ ከሶንበፍ ቀጥሎና ከ፪ኛው ሰኸምካሬ በፊት ነሪካሬ የሚባለው ፈርዖን ለአጭር ዘመን ነገሠ።
በእርሱ ዘመን የ14ኛው ሥርወ መንግሥት መጀመርያ ፈርዖን ያክቢም ሰኻኤንሬ በአባይ ወንዝ አፍ ዙሪያ ለእርሱ ተገዥ ሆኖ ነገሠ።
ቀዳሚው ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ | የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን 1816-1812 ዓክልበ. ግድም | ተከታይ ነሪካሬ |