ሙላቱ ተሾመ

ዶክተር ሙላቱ ተሾመኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ናቸው።

ሙላቱ ተሾመ
ተሾመ በ 2010
ተሾመ በ 2010
የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት
ከመስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ
ጠቅላይ ሚኒስትርኃይለማሪያም ደሳለኝ
ቀዳሚግርማ ወልደ ጊዮርጊስ
ተከታይሳህለወርቅ ዘውዴ
የኢትዮጵያ አምባሳደር በቱርክ
ከሚያዝያ ፲፫ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. እስከ መስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.
ተከታይአያሌው ጎበዜ
የግብርና ሚኒስትር
ከጥቅምት ፯ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. እስከ ሰኔ ፳፬ ቀን ፲፱፻፺፭ ዓ.ም.
ጠቅላይ ሚኒስትርመለስ ዜናዊ
ቀዳሚመንግሥቱ ሁሉካ
ተከታይአዲሱ ለገሰ
የተወለዱት፲፱፻፵፱ ዓ.ም.
አርጆ፣ ኢትዮጵያ
የፖለቲካ ፓርቲኦሕዴድ
ዜግነትኢትዮጵያዊ
ሀይማኖትየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና

ሙላቱ ተሾመ ውርቱ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ አርጆ ወረዳ በ1949 ዓ.ም. የተወለዱ ሲሆን የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርጆ እና በአዲስ አበባ ተከታትለዋል።

በ1974 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በፖለቲካ ኢኮኖሚ ፍልስፍና እንዲሁም በአለም አቀፍ ግንኙነት ከዚያም በፍልሰፍና የዶክቶሬት ድግሪያቸውን።

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በተለያዩ መስኮች ያከናወኑ እና በመምህርነትም ያገለገሉ ሲሆን ፥ አማርኛ ፣ ኦሮምኛ ፣ እንግሊዘኛ ፣ ቻይንኛ እንዲሁም ፈረንሳይኛ ቋንቋን መናገር እና መጻፍ ይችላሉ።

ከ1993-1994 ዓ.ም የኢፌዴሪ የግብርና ሚኒስትር ፣ ከጥቅምት 1994 እስከ 1998 ዓ.ም በፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት እንዲሁም ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በቱርክ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።

ዶክተር ሙላቱ በትዳር ህይወታቸው የአንድ ወንድ ልጅ አባት ናቸው።

ማመዛገቢያ

አዲሱ ፕሬዘደንት በብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል እየተደረገላቸው Archived ኦክቶበር 11, 2013 at the Wayback Machine