ሜሪላንድ


ሜሪላንድ (እንግሊዝኛ፦ Maryland) በአሜሪካ የምትገኝ ስቴት ስትሆን ምዕጻረ ቃሏ MD ወይም Md. ነው። ሜሪላንድ ከአሜሪካ አስራሶስት ጥንታዊ ስቴቶች አንዷ ናት። ከሜሪላንድ ጋር የሚገናኙ ስቴቶች ፔንስልቫኚያቨርጂኚያዌስት ቨርጂኚያ ፣ እና ዴላዌር እያሉ፤ ደግሞ በኮለምቢያ ክልል (ዋሽንግተን ዲ.ሲ.)ና በአትላንቲክ ውቂያኖስ ትወሰናለች። የቼሳፒክ ወሽመጥ ስቴቱን መሃል ለመሃል ይከፍለዋል። የሜሪላንድ ከፍተኛ ቦታ የባክቦን ተራራ ጫፍ ነው። የሜሪላንድ አየር ሁኔታ ከቦታ ቦታ ይለያያል። የምስራቅ ክፍሉ ሞቃታማ በጋና መካከለኛ ክረምት የአየር ሁኔታ ሲኖረው የምዕራብ ክፍሉ ደግሞ መካከለኛ በጋ እና በጣም ቀዝቃዛ ክረምት አለው። የሜሪላንድ ጠቅላላ ምርቶች በ2003 እ.ኤ.ኣ. ወደ 212 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚገመት ነው። በዚሁ ዓመት የአንድ ሰው የዓመታዊ ገቢ በኣማካይ 37,446 የአሜሪካን ዶላር ነበር ፣ ከአገሩ 5ኛ። ከፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ፣ ወታደራዊ ካምፖች እና የሳይንስና የሕክምና ተቋማት በዚሁ ክፍላገር ይገኛሉ። የስቴቱ ዋና ያውሮፕላን ማረፊያ ባልቲሞር-ዋሽንግተን ዓለም አቀፍ ያውሮፕላን ማረፊያ (BWI) ነው። በ1996 የሜሪላንድ ጠቅላላ የህዝብ ብዛት 5,558,058 ነው ተብሎ ይገመታል። ከዚሁ ውስጥም 583,900ቹ ወይም 10.6 በመቶ ሌላ ስቴት ወይም አገር የተወለዱ ነዋሪዎች ናቸው። አብዛኛው ህዝብ የስቴቱ መዓከላዊ ክፍል ውስጥ ይኖራል።

ሜሪላንድ ክፍላገር
የሜሪላንድ ባንዲራየሜሪላንድ ማኅተም
ዋና ከተማአናፖሊስ
ትልቋ ከተማባልቲሞር
አገረ ገዥማርቲን ኦማሊ
የመሬት ስፋት32,160 ካሬ ኪ.ሜ.(ከአገር 42ኛ)
የሕዝብ ብዛት5,296,486(ከአገር 19ኛ)
ወደ የአሜሪካ ሕብረት

የገባችበት ቀን

April 28,1788 እ.ኤ.ኣ.
ላቲቲዩድ (ኬክሮስ)37"53'N እስከ 39"43'N
ሎንግቲዩድ (ኬንትሮስ)75"4'W እስከ 79"33'W
ከፍተኛው ነጥብ1,024ሜ.
ዝቅተኛው ነጥብ0ሜ.
አማካኝ የመሬት ከፍታ105ሜ.
ምዕጻረ ቃልMD
ድረ ገጽwww.maryland.gov

ህዝብ

የህዝቡ የዘር ክፍልፋይ

  • 62.1%-ነጭ
  • 27.9%-ጥቁር
  • 4.3%-ላቲን
  • 4.0%-ኤሲያን
  • 0.3%-ቀይ ህንድ
  • 2.0%-ክልስ

የሐይማኖት ክፍልይ

  • ክርስቲያን-82%
    • ፕሮቴስታንት-56%
      • ባፕቲስት-18%
      • ሜቶዲስት-11%
      • ሌላ ፕሮቴስታንት-27%
    • ሮማን ካቶሊክ-23%
    • ሌላ ክሪስቲያን-3%
  • ይሁዳ-3%
  • ሌላ ሐይማኖት-15%

ታዋቂ ከተሞች

  • አናፖሊስ - የስቴቱ ዋና ከተማ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ባሕር ኃይል ማሰልጠኛ የሚገኝበት ቦታ
  • ባልቲሞር - በሕዝብ ብዛት ከስቴቱ አንደኛ
  • ኮሌጅ ፓርክ - ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሜሪላንድ የሚገኝበት ቦታ
  • ኮለምቢያ - ከስቴት 2ኛ ትልቅ ከተማ
  • ኦሽን ሲቲ - ታዋቂ የባሕር ዳር መዝናኛ (ቢች) ያለበት ሥፍራ
  • ሮክቪል - የሞንትጎምሪ ክልል (ካውንቲ) የንግድ ማዕከል
  • ሳሊስበሪ - የዴልማርቫ ልሳነ ምድር (ፔኒንሱላ) ትልቁ ከተማ እና የንግድ ማዕከል
  • ታውሰን - የባልቲሞር ክልል (ካውንቲ) መንግስት መቀመጫ

በሜሪላንድ ውስጥ የሚገኙ ክልሎች(ካውንቲዎች)

ካውንቲየተመሠረተበት ዓ.ም.(እ.ኤ.ኣ.)የመንግስት መቀመጫ
አለገኒ ካውንቲ1789ከምበርላንድ
አን አረንዴል ካውንቲ1650አናፖሊስ
ባልቲሞር ካውንቲ1659ታውሰን
ካልቨርት ካውንቲ1654ፕሪንስ ፍሬድሪክ
ካሮላይን ካውንቲ1773ዴንተን
ካሮል ካውንቲ1837ዌስትሚንስትር
ሲሲል ካውንቲ1672ኤልክተን
ቻርልስ ካውንቲ1658ላ ፕላታ
ዶርቸስተር ካውንቲ1668ኬምበሪጅ
ፍሬደሪክ ካውንቲ1748ፍሬደሪክ
ጋሬት ካውንቲ1872ኦክላንድ
ሀርፎርድ ካውንቲ1773ቤል ኤር
ሀዋርድ ካውንቲ1851ኤሊኮት ሲቲ
ኬንት ካውንቲ1642ቼስተር ታውን
ሞንትጎመሪ ካውንቲ1776ሮክቪል
ፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ1695አፐር ማርልቦሮ
ክዊን አን ካውንቲ1706ሴንተርቪል
ሴንት ሜሪ ካውንቲ1637ለናርድታውን
ሶመርሰት ካውንቲ1666ፕሪንስስ አን
ታልቦት ካውንቲ1662ኢስተን
ዋሽንግተን ካውንቲ1776ሄገርስታውን
ዊኮሚኮ ካውንቲ1867ሳሊስበሪ
ዎርስተር ካውንቲ1742ስኖው ሂል

ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች

  • ባልቲሞር ኸብሪው ዩኒቨርሲቲ
  • ባልቲሞር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ
  • ካፒቶል ኮሌጅ
  • ቼሳፒክ ኮሌጅ
  • ኮሌጅ ኦፍ ኖትር ዳም ኦፍ ሜሪላንድ
  • ኮለምቢያ ዩኒየን ኮሌጅ
  • ጋውቸር ኮሌጅ
  • ሁድ ኮሌጅ
  • ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ
  • ሎዮላ ኮሌጅ
  • ሜሪላንድ ኢንስትቲዩት ኮሌጅ ኦፍ አርት        
  • ማክዳንኤል ኮሌጅ
  • ሞንትጎምሪ ኮሌጅ
  • ሞርጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ
  • ማውንት ሴንት ሜሪ ዩኒቨርሲቲ
  • ሴንት ጆንሰ ኮሌጅ
  • ሴንት ሜሪ ኮሌጅ ኦፍ ሜሪላንድ
  • ሶውጆርነር-ዳግላስ ኮሌጅ
  • ዩኒፎርምድ ሰርቪስስ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ዘ ኸልዝ ሳየንስስ
  • ዩናይትድ ስቴትስ ኔቫል አካዳሚ
  • ቦዊ ስቴት ዩኒቨርሲቲ
  • ኮፒን ስቴት ዩኒቨርሲቲ
  • ፍሮስትበርግ ስቴት ዩኒቨርሲቲ
  • ሳሊስበሪ ዩኒቨርሲቲ
  • ታውሰን ዩኒቨርሲቲ
  • ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ባልቲሞር
  • ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሜሪላንድ
  • ዩኒቨርሲቲስ አት ሼዲ ግሮቭ
  • ዋሽንግተን ባይብል ኮሌጅ
  • ዋሽንግተን ኮሌጅ
  • ቪላ ጁሊ ኮሌጅ