ሰኔ ፳፱

(ከሰኔ 29 የተዛወረ)

ሰኔ ፳፱ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፪፻፺፱ ነኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፷፯ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፷፮ ቀናት ይቀራሉ።

አቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፰፻፸፯ ዓ/ም - ሉዊ ፓስተር የተባለው የፈረንሳይ ዜጋ በእብድ ውሻ በተለከፈው ጆሴፍ ማይስተር በተባለ ልጅ ላይ የውሻ ልክፍት መከላከያ ክትባቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ፈተነ።
  • ፲፱፻፶፰ ዓ/ም - ማላዊ ሪፑብሊክ ሆነች። ሄስቲንግስ ካሙዙ ባንዳ የመጀመሪያው ፕረዚደንት ሆኑ።
  • ፲፱፻፶፱ ዓ/ም - የናይጄሪያ ጦር ሠራዊት በአገሪቱ ደቡብ-ምሥራቅ የምትገኘውን የቢያፍራን ክልል ሲወሩ ለሦስት ዓመታት የተካሄደው የቢያፍራ ጦርነት ተከፈተ።

ልደት

  • ፲፱፻፳፯ ዓ/ም - አሥራ አራተኛው የቲቤት መንፈሳዊ መሪ ዳላይ ላማ፤ ጄትሱን ጃምፈል ንጋዋንግ ሎብሳንግ የሼ ቴንዚን ግያትሶ

ዕለተ ሞት

ዋቢ ምንጮች

  • (እንግሊዝኛ)P.R.O., FO 371/178551 Annual Review of 1963