ዓፄ በእደ ማርያም

(ከበእደ ማርያም የተዛወረ)

አጼ በእደ ማርያም በ፲፬፻፵ ዓ.ም ደብረ ብርሃን ከአባታቸው አጼ ዘርአ ያዕቆብና እናታቸው ጺዮን ምገሴ ተወልደው ከነሐሴ ፳፮፣ ፲፬፻፷ ዓ/ም - ኅዳር ፲፣ ፲፬፻፸ ዓ/ም የነገሡ የስሎሞናዊው ሥርወ መንግሥት አባል ናቸው። ዓፄ በእደ ማርያም፤ በተወለዱ በ ሠላሳ ዓመታቸው፤ በነገሡ በአሥር ዓመታቸው ባልታወቀ ህመም ሞቱ።

ዓፄ በእደ ማርያም
ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ
ግዛት፲፬፻፷ - ፲፬፻፸ .
ቀዳሚዘርአ ያዕቆብ
ተከታይዓፄ እስክንድር
ባለቤትካልዩፕ
ሥርወ-መንግሥትሰሎሞን
አባትዘርአ ያዕቆብ
እናትንግሥት ጽዮን ሞገሴ
የተወለዱት1440 ዓ.ም. ደብረ ብርሃን
የተቀበሩትአትሮንስ ማርያም
ሀይማኖትኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

ንጉሠ ነገሥት በእደ ማርያም ከላንቶ ይባል የነበረውን አገር አትሮንስ ማርያም ብለው ሰይመው፣ ቤተ ክርስቲያንም አሠርተው የማርያምን ታቦት አስገቡ። በዚህም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኒኮሎ ብራንካሌዮን በተባለ የቬኒስ ሰዓሊ የድንግል ማርያምና የሕጻኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስል አስለው ነበር። [1]

ማገናዘቢያ