ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 27

ጥቅምት ፳፯

  • ፲፰፻፯ ዓ.ም. -ሳክሶፎን የሙዚቃ መሣሪያ የፈጠረው የቤልጅግ ዜጋ አንቶን ጆሴፍ አዶልፍ ሳክስ በዚህ ዕለት ተወለደ።
  • ፲፰፻፹፮ ዓ.ም. - የክላሲክ ሙዚቃ ፈጣሪና አቀናባሪ የሩሲያው ዜጋ ፒተር ኢልዪች ቻይኮቭስኪ በፔትሮግራድ ከተማ አረፈ።
  • ፲፱፻፵፱ ዓ.ም. - የግብጽ ፕሬዚደንት ጋማል አብደል ናሰር በወቅቱ በብሪታንያ እና በፈረንሳይ ቁጥጥር ስር የነበረውን የሱዌዝ ቦይ የግብጽ ብሔራዊ ንብረት ሲያደርገው የብሪታንያና የፈረንሳይ ሰራዊቶች በቦዩ አካባቢ ግዛቶች ከግብጽ ሰራዊት ጋር ተዋጉ።
  • ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. - አምቺትካ ደሴት ላይ የአሜሪካ የአቶሚክ ኃይል ድርጅት በምድር ውስጥ “ካኒኪን” በሚል ቅጽል ስም የተሰየመውን ኃይለኛ የሃይድሮጅን ቦምብ በማፈንዳት ፈተሸ።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - አዲሱ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) አቶ አሀዱ ሳቡሬን የሐረርጌ ግዛት አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ።