የብርሃናት ክፍለ ዘመን
የብርሃናት ክፍለ ዘመን (ፈረንሳይኛ፦ le Siècle des Lumières /ለ ሲዬክል ዴ ሉምዬር/፣ ጀርመንኛ፦ Aufklärung /አውፍክላሩንግ/ «ማብራራት»፣ እንግሊዝኛ፦ Enlightenment /እንላይተንመንት/ «ማብራራት») በተለይ በ18ኛው ክፍለ ዘመን የተከሠተው፣ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን «ሳይንሳዊ አብዮት» የተከተለ የዘመናዊ ፍልስፍና እንቅስቃሴ ነበረ። «የፍልስፍና ክፍለ ዘመን» ወይም «የምክንያት ዘመን» ተብሏል።
እንቅስቃሴው የተጀመረው በፈረንሳይ ሲሆን፣ በተለምዶ ከ1707 እስከ 1781 ዓም ድረስ እንደ ቆየ ይቆጥሩታል። ከፈረንሳይ የ«ማብራራት» ሀሣቦች በተለይ ወደ እስፓንያ፣ ጀርመን፣ ፖላንድ፣ ሩስያ፣ ግሪክ፣ ስኮትላንድና አሜሪካ ተስፋፉ። በሌሎች አገራት ግን ለምሳሌ በእንግላንድ ወይም በጣልያን፣ «ማብራራቱ» አነስተኛ ሚና አጫወተ።
በዚህ ወቅት ዘመናዊ ከነበሩት ሃሣቦች መሃል፦
- ምክኑያዊነት
- የሳይንስ ፍልስፍና
- ጥቅማዊነት
- ለሴ ፈር
- ዴሞክራሲ
- እኩላዊነት
- ብሔራዊ መብቶች
- ሃይማኖታዊ መታገሥ
እንዲሁም በዚህ ወቅት የምጣኔ ሀብት፣ የሕገ መንግሥት፣ የአርነት፣ የትምህርት ፍልስፍናዎች እየተደረጁ ነበር። መደበኛ የክርክር ማህበር ሥርዓትና ቡና ቤት (ቡና የሚጠጣበት ሰዎችም የሚወያዩበት) ዘመናዊ ሆኑ። እንዲሁም የንጉሥ ወይም የፓፓ ሥልጣናት ተጽእኖ ይቀነስና ሕዝባዊነት፣ ተጠራጣሪነት ይበዛ ነበር።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |
🔥 Top keywords: ዋናው ገጽልዩ:Searchሥርዓተ ነጥቦችአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስኢትዮጵያየአድዋ ጦርነትየአክሱም ሐውልትአበበ ቢቂላዓፄ ቴዎድሮስጀጎል ግንብአማርኛአክሱምላሊበላቅዱስ ያሬድአፈወርቅ ተክሌአውሮፓየጋብቻ ሥነ-ስርዓትአርሰናል የእግር ኳስ ክለብኤችአይቪ2ኛው ዓለማዊ ጦርነትጥሩነሽ ዲባባጥላሁን ገሠሠእርዳታ:ይዞታትግራይ ክልልፕሮቴስታንትዳግማዊ ምኒልክመዝገበ ቃላትየኢትዮጵያ ነገሥታትሐረርዘጠኙ ቅዱሳንየኢትዮጵያ የ5 ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግውክፔዲያእምስሥነ-ፍጥረትዩ ቱብገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችአዲስ አበባመጽሐፍ ቅዱስግራኝ አህመድ