የቨርሳይ ውል

የቨርሳይ ውል (1911 ዓም) ከአንደኛው የዓለም ጦርነት ቀጥሎ ጀርመን ተሸንፎ ለአሸናፊዎቹ ሃያላት የተዋዋለው ስምምነት ውል ነበረ። የመንግሥታት ማኅበርም በዚህ ስምምነት ይቆም ጀመር።

የቨርሳይ ውል

አውሮፓም ሆነ በቅኝ አገራት በኩል፣ ከጀርመን መንግሥት ብዙ ርስት ተነሣባት።

በአውሮፓ

  • አልሳስ-ሎረን የተባለው ክፍል ወደ ፈረንሳይ ግዛት ተመለሰ።
  • ኦይፐን-ማልመዲ የተባለው ሰፈር ወደ ቤልጅግ ግዛት ተጨመረ።
  • ሽለስቭክ-ሖልሽታይን ዙሪያ ከሕዝብ ውሳኔ (1912 ዓም) ቀጥሎ ስሜኑ ወደ ዴንማርክ ተጨመረ።
  • ሕሉቺንስኮ የተባለው ሰፈር ወደ አዲሱ ቸኮስሎቫኪያ ግዛት ተሰጠ።
  • በሲሌስያ ዙሪያ ከሕዝብ ውሳኔ (1913 ዓም) ቀጥሎ ምሥራቁ ወደ አዲሱ ፖላንድ ግዛት ተጨመረ።
  • ከምዕራብ ፕሩሺያና ከፖዘን አውራጆች ብዙ መሬት ለፖላንድ ተሰጠ። ምሥራቅ ፕሩሺያ ክፍልን ከተረፈው ጀርመን የሚያስለይ «የፖላንድ መተላለፊያ» ተሰጠ።
  • ዳንፂክ ከተማ (የአሁኑ ግዳንስክ) በመንግሥታት ማህበር ሞግዚትነት ነጻ ከተማ-አገር ሆነ።
  • መመል የተባለው ዙሪያ ለጊዜው በመንግሥታት ማህበር ሞግዚትነትና በፈረንሳይ ሥራዊት ጥብቅና ሆነ፤ በ1915 ዓም ግን የሊቱዌኒያ ሃያላት ወደ ግዛታቸው ያዙት።
  • ዛዓር (ዛዓርላንት) የተባለው ክፍላገር ለጊዜው በአሸናፊ ሃያላት ሥራዊት አስተዳደር ሥር ሆነ። በ1927 ዓም ወደ ጀርመን (ናዚ ጀርመን) ተመለሰ።
  • በተጨማሪ የጀርመን ምዕራብ ራይንላንት ክፍል በአሸናፊ ሃያላት ሥራዊት አስተዳደር እስከ 1922 ዓም ድረስ ቆየ።

በቅኝ አገራትም

የጀርመን ቅኝ አገራት ሁሉ ወዲያው ወደ መንግሥት ማህበር ጥብቅና በሞግዚትነቶች ተሰጡ።

  • የርዋንዳ-ኡሩንዲ ክፍል ወደ ቤልጅግ ተዛወረ።
  • የኪዮንጋ ማዕዘን፣ በጣም አነስተኛ ሰፈር ወደ ፖርቱጋል ተዛወረ።
  • በጀርመን አስተዳደር የነበረችው ጪንግታው ከተማ በቻይና ውስጥ ወደ ጃፓን ተዛወረች።
  • ጀርመን ሳሞዓ የተባሉት ፓሲፊክ ደሴቶች ወደ ኒው ዚላንድ ተዛወሩ።
  • ጀርመን ኒው ጊኒ እና ናውሩ ደሴት ወደ አውስትራሊያ ተዛወሩ።
  • ከምድር ወገብ ስሜን የተቀመጡት ሌሎችም የተለያዩ የጀርመን ደሴቶች የደቡብ ፓሲፊክ ሞግዚትነት ተብሎ ወደ ጃፓን ተዛወሩ።

ከዚህም በላይ በጀርመን መንግሥት ላይ በጣም ትልቅ ካሳ ክፍያና እጅግ ብዙ አስቸጋሪ ቅጣት ድንጋጌዎች ተበዙበት። እነዚህ ከባድ ኹኔታዎች ለአዶልፍ ሂትለርና ለናዚ ጀርመን ጠንቅ እንደ ሆኑ ተብሏል።