ጥቅምት ፳፯

(ከጥቅምት 27 የተዛወረ)

ጥቅምት ፳፯ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፶፯ተኛው እና የመፀው ፴፪ተኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ በዘመነ ሉቃስ ፫፻፱ ቀናት ሲቀሩ፣ በዘመነ ዮሐንስ፤ ዘመነ ማቴዎስ እና ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፰ ቀናት ይቀራሉ።


ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፱፻፵፱ ዓ.ም. - የግብጽ ፕሬዚደንት ጋማል አብደል ናሰር በወቅቱ በብሪታንያ እና በፈረንሳይ ቁጥጥር ስር የነበረውን የሱዌዝ ቦይ የግብጽ ብሔራዊ ንብረት ሲያደርገው የብሪታንያና የፈረንሳይ ሰራዊቶች በቦዩ አካባቢ ግዛቶች ከግብጽ ሰራዊት ጋር ተዋጉ።
  • ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. - አምቺትካ ደሴት ላይ የአሜሪካ የአቶሚክ ኃይል ድርጅት በምድር ውስጥ “ካኒኪን” በሚል ቅጽል ስም የተሰየመውን ኃይለኛ የሃይድሮጅን ቦምብ በማፈንዳት ፈተሸ።
  • ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - አዲሱ የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት (ደርግ) አቶ አሀዱ ሳቡሬን የሐረርጌ ግዛት አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ።


ልደት

  • ፲፰፻፯ ዓ.ም. -ሳክሶፎን የሙዚቃ መሣሪያ የፈጠረው የቤልጅግ ዜጋ አንቶን ጆሴፍ አዶልፍ ሳክስ


ዕለተ ሞት

  • ፲፰፻፹፮ ዓ.ም. - የክላሲክ ሙዚቃ ፈጣሪና አቀናባሪ የሩሲያው ዜጋ ፒተር ኢልዪች ቻይኮቭስኪ በፔትሮግራድ ከተማ አረፈ።


ዋቢ ምንጮች

  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FO 371/154836 - Annual Report from Ethiopia for 1960
  • (እንግሊዝኛ) P.R.O., FCO 371/536 Annual Review of 1969


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ