ስምንት

ስምንት በተራ አቆጣጠር ከሰባት የሚከተለው ቁጥር ነው።

ምልክቱ ከግዕዝ እንደ ተወረሰ ነው፣ ይህም ከግሪክ አልፋቤት ፊደል ኤታ (በትንሹ «Η η») እንደ ተወሰደ ይታመናል።

ከሕንዳዊ ላሳናት 8 ምልክቶች ወደ ዘመናዊ «8» የደረሱ ለውጦች።

በብዙ ልሳናት የሚገኘው ምልክት 8 ከሕንዳዊ ቁጥር ምልክቶች ተደረጀ። እነዚህ ምልክቶች በአውሮፓ ከ968 እና 1550 ዓም መካከል እየተደረጁ ተቀባይነት አገኙ። ከዚያ አስቀድሞ በሮማውያን ቁጥር ምልክቶች የ«ስምንት» ምልክት «VIII» (ወይም viij) ነበር።