ታገስ ወንዝ

ታገስ ወንዝ (እስፓንኛ፦ Tajo /ታሖ/፤ ፖርቱጊዝኛ፦ Tejo /ቴኁ/) በአውሮፓ ውስጥ የሚገኝ ታላቅ ወንዝ ነው። ይህ ወንዝ 1,006 ኪ.ሜ. ያህል የሚረዝም ሲሆን ዓለማችን ከሚገኙ ወንዞች 173ኛ ረዥሙ ወንዝ ነው። ወንዙ በዚህ ርዝመቱ ስፔን እና ፖርቹጋል ውስጥ 80,100 ኪ.ሜ. ካሬ ያህል ስፋት ያካልላል። ይህንን ያህል ርዝመት እና ስፋት በሀገራቱ ላይ ካካለለ በኋላ የወንዙ መዳረሻ አትላንቲክ ውቅያኖስ ነው።

ታገስ ወንዝ
የታገስ ወንዝ ካርታ
የታገስ ወንዝ ካርታ
መነሻፍዌንቴ ዴ ጋርሲያ
መድረሻሊስቦን
ተፋሰስ ሀገራትስፔንፖርቱጋል
ርዝመት1,038 ኪ/ሜ (645 ማይል)
የምንጭ ከፍታ0 ሜ
አማካይ ፍሳሽ መጠንመካከለኛ : 500 m³/s
የተፋሰስ አካባቢ ስፋት80,100 km²