ነጨሪኸት
ነጨሪኸት (ወይም ጆሠር) በጥንታዊ ግብጽ የነገሠ ፈርዖን ነበረ። ሹሙ እምሖተፕ መጀመርያውን ሀረም (ፒራሚድ) በሳቃራ እንዲገነባ ያዘዘው እሱ ነበር። የዘመኑ አመታት ጊዜ ልክ ባይታወቅም ምናልባት በ2982 አክልበ. የሚያሕል ነበር።
የሱ መቃበር ሀረም ከሁሉ አስቀድሞ የተገነባው ሀረም ሲሆን ከተደረቡ ደረጃዎች ተሠራ እንጂ እንደ ኋለኞቹ ሀረሞች ቅርጽ አልነበረም። በዚህ ወቅት በግዮን ሸለቆ የኖሩት ሕዝቦች የነገሥታትን ሕንጻዎች በግድ ይሠሩ ጀመር።
ነጨሪኸት ደግሞ ዘመቻ በሲና አካባቢ አድርጎ፣ በዚያ በአለት በተቀረጸው ጽሕፈት የሴት ወገንና የሔሩ ወገን ምልክቶች ይታያሉ። ከነጨሪኸት በፊት የነገሡት ፈርዖኖች ፐርብሰንና ኃሠኸምዊ የሴት ወገን ምልክት ወደ አርማቸው ጨምረው ቢሆንም፣ የነጨሪኸት አርማ (ሰረኽ) ግን የሔሩ ምልክት (ጭላት) ብቻ አሳየ።
🔥 Top keywords: ዋናው ገጽልዩ:Searchሥርዓተ ነጥቦችአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስኢትዮጵያየአድዋ ጦርነትየአክሱም ሐውልትአበበ ቢቂላዓፄ ቴዎድሮስጀጎል ግንብአማርኛአክሱምላሊበላቅዱስ ያሬድአፈወርቅ ተክሌአውሮፓየጋብቻ ሥነ-ስርዓትአርሰናል የእግር ኳስ ክለብኤችአይቪ2ኛው ዓለማዊ ጦርነትጥሩነሽ ዲባባጥላሁን ገሠሠእርዳታ:ይዞታትግራይ ክልልፕሮቴስታንትዳግማዊ ምኒልክመዝገበ ቃላትየኢትዮጵያ ነገሥታትሐረርዘጠኙ ቅዱሳንየኢትዮጵያ የ5 ሺ ዓመት ታሪክ ከኖኅ እስከ ኢህአዴግውክፔዲያእምስሥነ-ፍጥረትዩ ቱብገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞችአዲስ አበባመጽሐፍ ቅዱስግራኝ አህመድ