Jump to contentውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 21
ኅዳር ፳፩
- ፲፱፻፵፮ ዓ.ም. በኡጋንዳ የቡጋንዳ ንጉሥ ዳግማዊ ኤድዋርድ ሙቴሳ በአገሪቱ የብሪታንያ አስተዳደሪ ‘ሰር አንድሩው ኮሄን’ ተሽረው በስደት ወደ ለንደን ሄዱ።
- ፲፱፻፷ ዓ.ም. የየመን ሕዝባዊ ሪፑብሊክ ከብሪታንያ ነጻነቷን ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፷ ዓ.ም. በፓኪስታን በኋላ የአገሪቱ መሪ የሆኑት እና በወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ወርደው በስቅለት ሞት የተቀጡት ዙልፊቃር አሊ ቡቶ የፓኪስታን ሕዝባዊ ፓርቲን መሠረቱ።
- ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. በካምፓላ ኡጋንዳ የተወለዱት ጆን ታከር ሙጋቢ ሴንታሙ ዘጠና ሰባተኛው የዮርክ ሊቀ ጳጳስ ሆኑ። በዚህ ቤተ ክርስቲያን ይሄንን ታላቅ ሥልጣን የተቀበሉት የመጀመሪያው ጥቁር ጳጳስ ናቸው።