ላይቤሪያ


ላይቤሪያ (እንግሊዝኛLiberia)፣ በይፋ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ (እንግሊዝኛ፦ Republic of Liberia)፣ በምዕራብ አፍሪካ የምትገኝ ሀገር ናት። በጊኒኮት ዲቯርሴራሊዮን እና በአትላንቲክ ውቅያኖስ ትዋሰናለች። ላይቤሪያ የቅኝ ግዛት ሆና በ1822 እ.ኤ.አ. ከአሜሪካ በመጡ ነጻ የወጡ ባሪያዎች የተመሠረተች ሲሆን በአካባቢው ግን የተለያዩ ብሔሮች ለብዙ ምእተ አመታት ኖረዋል። መሥራቾቹ ዋና ከተማቸውን ሞንሮቪያ ብለው ለአሜሪካን ፕሬዝዳንት ጄምስ ሞንሮው ሰይመውታል። ሐምሌ ፳ ቀን ፲፰፻፴፱ ዓ/ም ነጻነት አወጁና ግዛቷ የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ሆነች። በ1980 እ.ኤ.አ. በወታደራዊ መፈንቅለ-መንግስት የላይቤሪያ አመራር ከወረደ በኋላ ከ1989 እስከ 2005 እ.ኤ.አ. ድረስ ሀገሩዋ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ያፈናቀሉና የሀገሩዋን ኢኮኖሚ ያቃወሱ ሁለት የእርስ-በርስ ጦርነቶችን አይታለች።

የላይቤሪያ ሪፐብሊክ
Republic of Liberia

የላይቤሪያ ሰንደቅ ዓላማ የላይቤሪያ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር ኦል ሄል፣ ላይቤሪያ፣ ሄል!
እንግሊዝኛ፦ All Hail, Liberia, Hail!
የላይቤሪያመገኛ
የላይቤሪያመገኛ
ላይቤሪያ በቀይ ቀለም
ዋና ከተማሞንሮቪያ
ብሔራዊ ቋንቋዎችእንግሊዝኛ
መንግሥት
ፕሬዝዳንት
ምክትል ፕሬዝዳንት
ሪፐብሊክ
ጆርጅ ዌያ
ጁወል ተይለር
ዋና ቀናት
ሐምሌ ፳ ቀን ፲፰፻፴፱ ዓ/ም
(July 26, 1847 እ.ኤ.አ.)
 
የነጻነት ቀን
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
111,369 (103ኛ)
13.514
የሕዝብ ብዛት
የ2008 እ.ኤ.አ. ግምት
የ2005 እ.ኤ.አ. ቆጠራ
 
3,489,072 (132ኛ)
3,482,211
ገንዘብየላይቤሪያ ዶላር1
ሰዓት ክልልUTC +0
የስልክ መግቢያ231
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ.lr
1. የአሜሪካ ዶላርም በሰፊ ጥቅም ላይ ነው

የስም አመጣጥ

«ላይቤሪያ» ከእንግሊዝኛው liberty (ሊበርቲ፣ ማለትም ነጻነት) ከሚለው ቃል ነው የመጣው።

ታሪክ

የምዕራብ አፍሪካ አገሬዎች (ተወላጆች)

የአንትሮፖሎጂ ምርምር እንደሚያሳየው ከሆነ፣ በላይቤሪያ ላይ ከ12ኛው ክፍለ-ዘመን ወይም ከዛ በፊት ጀምሮ ሰው ሠፍሯል። መንዴ (Mende) የሚባል ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ወደ ምዕራብ ሲስፋፉ፣ ሌሎች ታናናሽ ብሄረሰቦችን ወደ ደቡብ ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ገፍተዋቸዋል። ዴዪ፣ ባሳ፣ ክሩ፣ ጎላ እና ኪሲ የሚባሉ ጎሳዎች በአካባቢው ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደነበሩ በማስረጃ ይታወቃል። ይህ ፍልሰት የጨመረው የማሊ ግዛት በ1375 እ.ኤ.አ. እና የሶንጋይ ግዛት በ1591 እ.ኤ.አ. ሲዳከሙ ነው። በተጨማሪም ወደ ውስጥ ያለው ሥፍራ ወደ በርሃነት እየተለወጠ ስለመጣ፣ ነዋሪዎቹ ወደ እርጥቡ ፔፐር ጠረፍ (Pepper Coast) እንዲሄዱ ተገደዱ። ከማሊና ሶንጋይ ግዛቶች የመጡ አዳዲስ ነዋሪዎች ጥጥ ማሽከርከር፣ ልብስ መስፋት፣ ብረት ማቅለጥ እና ሩዝና ማሽላ ማብቀልን የመሳሰሉ ጥበቦች ለቦታው አስተዋወቁ።

የላይቤሪያ አገሬ ሴቶች በ1910 እ.ኤ.አ.

መኔ ሰዎች (ከመንዴ ወታደሮች የመጡ) አካባቢውን ከተቆጣጠሩ በኋላ ቫይ የሚባል የማሊ ግዛት ከፈረሰ በኋላ ለመሰደድ የተገደደ ብሔር ወደ ግራንድ ኬፕ ማውንት (Grand Cape Mount) የሚባለው ሥፍራ ፈለሱ። የክሩ ብሔር የቫይን ፍልሰት ተቃወሙ። ከመኔ ብሔር ጋር አንድ ላይ በመሆንም የቫይ ብሔርን ከግራንድ ኬፕ ማውንት አልፈው እንዳይስፋፉ አገዱ።

በጠረፍ ላይ የሚኖሩት ሰዎች ታንኳ ሰርተው ከካፕ-ቨርት እስከ የወርቅ ጠረፍ (Gold Coast) ድረስ ካሉት ሌሎች ምዕራብ አፍሪካውያን ጋር ይገበያዩ ነበር። የክሩ ጎሳ በመጀመሪያ ለአውሮፓውያን ሰው ያልሆኑ ነገሮችን ይሸጡ ነበር። ግን በኋላ በየአፍሪካ ባሪያ ንግድ ውስጥ መሳተፍ ጀመሩ።

የክሩ ሠራተኞች ቦታቸውን ትተው በትልቅ እርሻዎችና የግንባታ ሥራዎች ላይ ተሳትፈዋል። አንዳንዶቹም የስዊዝና ፓናማ መስኖዎች ለመገንባት ረድተዋል።

ሌላ ግሌቦ የሚባሉ ሰዎች የመኔ ጎሳ አካባቢያቸውን ሲወር፣ በኋላ የላይቤሪያ ወደ ሚሆነው ጠረፍ አመሩ።

የቀድሞ የአውሮፓውያን ግንኙነት

በ1461 እ.ኤ.አ. እና 17ኛው ክፍለ-ዘመን መጨረሻ መካከል ፖርቱጋላዊ፣ ሆላንዳዊና ብራታንያዊ ነጋዴዎች በላይቤሪያ የንግድ ቦታ አቋቁመው ነበር። በተጨማሪም የአንድ የሚጥሚጣ አይነት ፍሬ በመብዛቱ ፖርቱጋላዊያን አካባቢውን Costa da Pimenta (ኮስታ ዳ ፒሜንታ) ማለትም የፍሬ ጠረፍ ብለው ሰይመውት ነበር።

ከአሜሪካ የመጡ ሰፋሪዎች

በ1822 እ.ኤ.አ. የአሜሪካ የቅኝ መግዛት ማህበር ላይቤሪያን ባሪያ የነበሩ ጥቁር ሰዎች የሚላኩበት ቦታ አድርጎ አቋቋመ። ከሌሎች ባሪያ ያልነበሩ ጥቁር አሜሪካውያንም ወደ ላይቤሪያ ለመሄድ የመረጡ ነበሩ። ወደ እዛ የሄዱት አሜሪካዊ ላቤሪያዊያን በመባል ይታወቃሉ። በሐምሌ 20 ቀን 1839 ዓ.ም. እነዚህ ሰፋሪዎች የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ነፃነትን አወጁ።

የአመራር ክፍሎች

የላይቤሪያ የአመራር ክፍሎች
ቁጥርየአገዛዝ ክፍልየሕዝብ ብዛት (2008 እ.ኤ.አ.)[1]ስፋት (ካሬ ኪ.ሜ.)[1]የተፈጠረው (እ.ኤ.አ.)
1ቦሚ82,0361942
2ቦንግ328,91987721964
3ግባርፖሉ83,75896892001
4ግራንድ ባሳ224,8397936
5ግራንድ ኬፕ ማውንት129,0555162
6ግራንድ ጌዴህ126,146104841964
7ግራንድ ክሩ57,10638951984
8ሎፋ270,11499821964
9ማርጊቢ199,6892616
10ሜሪላንድ136,40422971857
11ሞንትሴራዶ1,144,80619091847
12ኒምባ468,088115511964
13ሪቨር ሴስ65,8625594
14ሪቨር ጂ67,31851132000
15ሲኑ104,932101371847

ሀይማኖት

አርባ ከመቶ የሚሆነው የሀገሩ ሕዝብ ክርስቲያን ነው። ሌላ ሀያ ከመቶ የሚሆን ሕዝብ የራሱ የአገሬው ሀይማኖት አለው። የቀረው አርባ ከመቶ ሕዝብ የእስልምና እምነት ተከታይ ነው።

ትምህርት

ተማሪዎች በሻማ ብርሃን ሲያጠኑ፣ ቦንግ የአገዛዝ ክፍል፣ ላይቤሪያ

የላይቤሪያ ዩኒቨርሲቲ በሞንሮቪያ ይገኛል። በ1862 እ.ኤ.አ. የተከፈተ ሲሆን ከአፍሪካ ቀደምት የከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አንዱ ነው። በእርስ-በርስ ጦርነት ጊዜ በጣም የተጎዳ ሲሆን አሁን እንደገና እየተገነባ ነው።

ከቲንግተን ዩኒቨርሲቲ በየአሜሪካ ኢጲስ ቆጶስ ቤተክርስቲያን በ1889 እ.ኤ.አ. ተመሥርቷል። ግቢው በሱዋኮኮ፣ ቦንግ የአገዛዝ ክፍል ይገኛል።

ነጥቦች

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ ላይቤሪያ የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።