የመስቀል ጦርነቶች

የመስቀል ጦርነት

የመስቀል ጦርነቶች


ዓለም ከአስተናገደቻቸው አስከፊና አሰቃቂ የፓለቲካ፣ የዳርድንበር እንዲሁም የዘር ጦርነቶች ባልተናነሰ የአይማኖት ጦርነቶችንም አስተናግዳለች።ስስና አይነኬ በመባል በሚጠራው የአይማኖት ጉዳይ አማካኝነት ወንድም ከወንድሙ፣እህትም ከእህቶ ሳይቀር ጎራበመክፈል እርስበርሳቸው ደም ተፋሰዋል።በዚህች የሰው ልጆች እንደመኖሪያ ቤታችን በምንጠቀምባት ዓለም ውስጥ ብዙ አስከፊና መራራ የአይማኖት ጦርነቶችየተካሄዱባት ሲሆን ከነሱም ውስጥ የመስቀል ጦርነት(Crusade) በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት በሆላ ከ1095 እስከ 1204 ባሉት109 አመታት ውስጥ 4 የመስቀል ጦርነቶች የተደረጉ ሲሆንበነዚህም ጦርነቶች አማካኝነት ከ5 ሚሊየን ያላነሰህዝብ ህይወቱን አጥቶል።እነዚህ የመስቀል ጦርነቶች አብዛኞቹ በዘመኑ በነበሩ የአይማኖት አባቶች ወይም ጳጳሳት አማካኝነት የተመሩ ሲሆንለጳጳሳቱ ወደn ጦርነት መግባት እንደምክንያት ሆኖ የሚጠቀሰውበታላቁ መፅሐፍ ወይም በመፅሐፍ-ቅዱስ ውስጥ ቅድስቲቶ ምድር (holly land) ተብላ የተጠቀሰችውን እየሩሳሌምንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ከተሞችን ከወራሪዎችእጅ ለመንጠቅ በሚል ነው።በነዚህ ተከታታይ 4 የመስቀል ጦርነትቶች ውስጥ የመስቀል

ጦረኞች በማን ተመሩ? አላማቸውስ ምነበር? እንዴትስ ተጠ

ናቀቀ? የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ከዚህ በታችባጭሩ እንያቸው።


አንደኛው የመስቀል ጦርነት

በPope Urban 2ኛ፣ Walter The Penniless እንዲሁም በPeter The Hermite በጋራ በተካሄደው የመጀመርያው የመስቀል ጦርነት 1095 እስከ 1099 ለ4አመታት የፈጀ ሲሆን አላማቸውም አንቲያክንና እየሩሳሌምንይዞ የመስቀል ጦር ግዛቶች ማድረግ ነበር ይህም አላማቸው ሰርቶ ጦርነቱን በአሸናፊነት አጠናቅቀዋል።


ሁለተኛው የመስቀል ጦርነት

በPope Eugenus 3ኛ፣ በEmperor Konrad 3ኛ፣በLouis 5ኛ እንዲሁም በBerard of clarivaux ትብብርየተደረገው ሁለተኛው የመስቀልጦርነት ከ1147 አስከ 1149 የፈጀ ሲሆን አላማውም በሙስሊም ጦረኞች ግዛት ስር የነበረችውን የኤዳሰን ከተማንለመያዝ ነበር። ነገር ግን በጦርነቱ በመሸነፋቸው አላማቸው ሳይሰምር ቀርቶል አልፎ ተርፎ ቀድሞ በቁጥጥራቸው ስር የነበሩትን ከተሞችንም አጥተዋል


ሶስተኛ የመስቀል ጦርነት

ይሄ ሶስተኛው የመስቀል ጦርነት በወቅቱ ስማቸው ገኖ በነበረው የጦር ሜዳ ጀግኖች በነ Richard The lion-Hearted፣ በEmperor Fredic Barbarossa፣ በphilip Augutus እና King of Frace ቅንጅትከ1189 እስከ 1192 የተደረገ ጦርነት ሲሆን። በSaladin እጅስር የገባችውን እየሩሳሌም ዳግምለማስመለስ የታቀደ ጦርነት ነበር። ምንም እኳን ክሩሴደሮቹ ሙስሊሞችን በሁሉም ውጊያዎች ቢያሸንፉም፤ ንጉሱ ሪቻርድ አውሮፓ ውስጥ የተፈጠረን አመፅ ለማስቆም ሲመለስ ውጊየው በመቆሙ ወደ ከተማይቱ ሳይገቡ ቀርተዋል።


አራተኛው የመስቀል ጦርነት

በ1198 በpope innocent II አማካኝነት የተጠረውና በፈረንሳይ የመስቀል ጦረኞች የተሳተፋበት ከ1202 እስከ 1204 የፈጀው 4ኛው የመስቀል ጦርነትክርስትያኖችን የኋይልና የሞራል ውድቀት ላይ ጥሎ ነው ያለፈው። የሙስሊሞችን ኋይል ከእስራሄልና ከአጎራባች አገሮችማስወጣት ዓላማው አርጎ የተነሳውይህ አራተኛው የመስቀል ጦርነት እንዳሰቡት ሳይሳካ ከመጠናቀቁ በላይ በቁጥጥራቸው ስር የነበሩትን የኮንስታንቲኖፕል(Constantinople) እና የዛራ(Zara) ግዛቶችአጥተውበታል።

ምንጭ => www.lemenemesekelasefelege.blogspot.com/2017/12/images-1jpg.html?m=1