የቻይና ነገሥታት ዝርዝር

ማስታወሻ፦ በቻይና ታሪክ ከ849 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት አስቀድሞ የሆኑት አመት ቁጥሮች ሁሉ አጠያያቂ ናቸው። ከ849 ዓክልበ. በኋላ ግን አመቶቹ በብዛት ሊወሰኑ ይቻላል። ከሥነ ቅርስ መጀመርያው የተረጋገጠው ንጉሥ ዉ ዲንግ ነው። ከ1200 ዓክልበ. የሆኑት ንግርተኛ አጥንቶች ጽሑፎች በኤሊ ቅርፊት ወይም በበሬ ትከሻ ላይ የጨረቃ ግርዶሽ ጊዜዎች ስለ ዘገቡ፣ የቻይና አጥኒዎች የዉ ዲንግን ዘመን ልክ ከ1258-1199 ዓክልበ. ወስነውታል።

አፈ ታሪካዊ ዘመን

  1. ኒዋ - የፉሢ ሚስት፣ ከማየ አይኅ አመለጠች
  2. ዮውቻው - ቤትን ማገንባት ያገኘ
  3. ስዊረን - የእሳት ጥቅም ያገኘ
  4. ፉሢ - ከሚስቱ ከኒዋ ጋራ ከማየ አይኅ አመለጠ። ከዚያ 115 ወይም 116 ዓመት እንደ ነገሠ ይባላል።
  5. «የነበልባል ነገሥታት» ፦ ሸንኖንግ (38 አመት)፣ ሊንኲ፣ ቸንግ፣ ሚንግ፣ ዥዕ፣ ከ፣ አይ፣ ዩዋንግ - 500 ዓመታት ያህል በጠቅላላ ይባላል

የኋሥያ ነገሥታት (አፈታሪካዊ፣ 2389-2010 ዓክልበ. ግድም)

  1. ኋንግ ዲ (ጎንግሱን ሽወንዩወን) - የዮሾንግ መሪ፣ ያንዲ ዩዋንግን በባንጯን ውግያ አሸንፎ ዮሾንግንና ሸንኖንግን በኋሥያ አዋሀደ። 99 ዓመት ነግሠ።
  2. ሻውሃው - 84 አመት ነገሠ? (በቀርከሃ ዜና መዋዕል ዘንድ ምናልባት 7 ዓመት ብቻ ነገሠ)
  3. ዧንሡ - 78 አመት ነገሠ። የኅብረተሠብ ማሻሻሎች ሠራ
  4. ዲ ኩ - 60 ወይም 70 አመት ነገሠ (63 በቀርከሃ ዜና መዋዕል)፤ ትምህርት ቤቶች ሠራ
  5. ዲ ዥዕ - 9 ዓመት
  6. ያው - 99 አመት ነገሠ (በ73ኛው አመት ዙፋኑን ለተከታዩ ሹን መልቀቁን በቀርከሃ ዜና መዋዕል ይዘገባል)
  7. ሹን - 50 ዓመት፤ ሕግ አወጣ

የሥያ ሥርወ መንግሥት (2010-1611 ዓክልበ. ግድም)

የሻንግ ሥርወ መንግሥት (1611-1054 ዓክልበ ግድም)

የዦው ሥርወ መንግሥት (1054-229 ዓክልበ.

የጪን ሥርወ መንግሥት (229-214 ዓክልበ.)

የሃን ሥርወ መንግሥት (214 ዓክልበ. - 212 ዓ.ም.)