ሁለት

ሁለት በተራ አቆጣጠር ከአንድ የሚከተለው ቁጥር ነው።

ምልክቱ ከግዕዝ እንደ ትወረሰ ነው፣ ይህም ከግሪክ አልፋቤት ፪ኛው ፊደል ቤታ (በትንሹ «β») እንደ ተወሰደ ይታመናል።

ከሕንዳዊ ላሳናት 2 ምልክቶች ወደ ዘመናዊ «2» የደረሱ ለውጦች።

በብዙ ልሳናት የሚገኘው ምልክት 2 ከሕንዳዊ ቁጥር ምልክቶች ተደረጀ። እነዚህ ምልክቶች በአውሮፓ ከ968 እና 1550 ዓም መካከል እየተደረጁ ተቀባይነት አገኙ። ከዚያ አስቀድሞ በሮማውያን ቁጥር ምልክቶች የ«ሁለት» ምልክት «II» (ወይም «ij») ነበር።