መቶ

መቶ ወይም አንድ መቶ በተራ አቆጣጠር ከዘጠና ዘጠኝ የሚከተለው ቁጥር ነው።

ምልክቱ ከግዕዝ እንደ ተወረሰ ነው፣ ይህም ከግሪክ አልፋቤት ፊደል ሮ («Ρ፣ ρ») እንደ ተወሰደ ይታመናል።

በብዙ ልሳናት የሚገኘው ምልክት 100 ከሕንዳዊ ቁጥር ምልክቶች 1 አንድ እና 0 ዜሮ ተደረጀ። ከዚያ አስቀድሞ በሮማውያን ቁጥር ምልክቶች የ«መቶ» ምልክት «C» ነበር።