ማይክሮሶፍት

ማይክሮሶፍት ኮርፖሬሽን ዓለም-አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅት ነው። እንደ ጁላይ 2006 እ.ኤ.አ. ማይክሮሶፍት 71,553 ሠራተኞች በ102 ሀገሮች ሲኖረው፣ ዓመታዊ ገቢው 44.28 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ነው። እጅግ በጣም ብዙ የሚሆኑ ሶፍትዌሮችን ማምረትና ማዳበር ዋና ዓላማው ነው። ዋና መስሪያቤቱ በሬድመንድ፣ ዋሽንግተን፣ አሜሪካ የሚገኝ ሲሆን፣ ታዋቂ ምርቶቹ ማይክሮሶፍት ዊንዶውስ ስርአተ ክወና እና ማይክርሶፍት ኦፊስ ግሴት ሶፍትዌር ያጠቃልላሉ። ከሶፍትዌሮች ሌላ፥ ኤም.ኤስ.ኤን.ቢ.ሲ የኬብል ቴሌቪዥን፥ ኤም.ኤስ.ኤን. ዌብሳይት፥ ማይክሮሶፍት ኢንካርታ የኢንተርኔት መዝገበ ዕውቀት፥ የቤት መዝናኛ እና ሌሎችም ምርቶችና አገልግሎቶችን ያቀርባል።

ኢንዱስትሪኮምፒዩተር ሶፍትዌር
ኮምፒዩተር ሐርድዌር
ቴሌቪዥን
ምርምርና ማዳበር
ኢንተርኔት
ገቢ$44.28 ቢሊዮን (2006 እ.ኤ.አ.)
ቅርንጫፎች{{{ድህረገፅ}}}