ቁርቁራ

ቁርቁራ (Ziziphus mauritiana) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ተክል ነው።

ቁርቁራ

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ

ቊጥቋጥ ወይም አነስተኛ ዛፍ እስከ 6 ሜትር ይደርሳል።

(በአንድ ጥናት ዘንድ፣ የእህቱ ዝርያ Ziziphus spina-christi «ቁርቁራ» ወይም ጌባ ተብላለች።)

አስተዳደግ

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር

ባጠቃላይ እንደ ቆላ ቊጥቋጥ ይገኛል።

የተክሉ ጥቅም

የደረቀው እንጨት በሶማሌ ሴቶች ጸጉራቸውን ለማጠን ይጠቀማል።

በአንዳንድ ቦታ ልጡ እንደ አሳ መርዝ ተጠቅሟል።

ሥሮቹ ቁርጥ አድርጎ የሚስብና ያንገት ነቀርሳ (ስክሮፉላ) ለማከም የሚችል ጥንተ ንጥር ሊኖራቸው ይቻላል።

ፍሬው ቢበላም አማረ ጌታሁን (በ1976 እ.ኤ.አ.) እንደ ጻፉ ልጆች ብቻ እንደ በሉት መሰላቸው። በቆላ ግን ያደጉትም ሰዎች እንደ በሉት ጨመሩ። ልጆችም ዘሮቹን ለዶቃዎች መጠቀማቸውን መሰከሩ።

ቀዩ እንጨት ውድ ነው፤ በእሳት ላይ ጢስን ለመስጠት ይጠቀማል።[1]