ብሬመን ክፍላገር

ብሬመን ክፍላገር (ጀርመንኛ፦ Freie Hansestadt Bremen «የብሬመን ነጻ ሃንሳዊ ከተማ») ከጀርመን ክፍላገራት ከሁሉ ታናሽ ሲሆን ሁለት ከተሞች ብቻ ነው እነርሱም ብሬመንና ብሬመርሃቭን ናቸው። ሁለቱ ከተሞች ቅጥልጥል ሳይሆኑ በትንሽ ርቀት ተለይተዋል።

«Hansestadt» ወይም «ሃንሳዊ ከተማ» ማለት በድሮ ታሪክ የሃንሳ ትብብር የከተሞች ንግድ ትብብር አንድ አባል ስለ ነበር ነው።