የዕምባዎች ጎዳና

የዕምባዎች ጎዳና ከ1823 ዓ.ም. እስከ 1830 ዓ.ም. የአሜሪካ መንግሥት ኗሪ ጎሣዎችን ('ቀይ ሕንድ' የተባሉ) ከአገር ቤታቸው በግድ አስነቅሎ እስከ ኦክላሆማ ያሳደዳቸውበት መንገድ ነበር። እነዚህ ኗሪ ብሔሮች ቾክታው፣ ሴሚኖል፣ ክሪክ፣ ቺካሳው እና ቼሮኪ ናቸው። በመንገዳቸው ላይ ብዙ ኗሪዎች ከበሽታ ወይም ከረሃብ ጠፉ።

የኗሪ ብሔሮች ወደ ኦክላሆማ ስደት ከ1830 እስከ 1835 እ.ኤ.አ. የሚያሳይ ካርታ