ሃይቲ


ሃይቲካሪቢያን ባሕር ውስጥ ሂስፓንዮላ በተባለ ደሴት ላይ የሚገኝ አገር ነው። ዋን ከተማው ፖርቶፕሪንስ ሲሆን መደበኛ ቋንቋዎች ፈረንሳይኛ እና የሃይቲ ክሬዮል ናቸው።

ሃይቲ ሪፐብሊክ
République d'Haïti
Repiblik Ayiti

የሃይቲ ሰንደቅ ዓላማ የሃይቲ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር La Dessalinienne

የሃይቲመገኛ
የሃይቲመገኛ
ዋና ከተማፖርቶፕሪንስ
ብሔራዊ ቋንቋዎችፈረንሳይኛ
የሃይቲ ክሬዮል
መንግሥት
ፕሬዝዳንት
ጠቅላይ ሚኒስትር
ፕሬዚዳንታዊ ሪፐብሊክ
ዦቨነል ሞይዝ
ዣክ ጊ ላፎንታንት
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
27,750 (140ኛ)
0.7
የሕዝብ ብዛት
የ2015 እ.ኤ.አ. ግምት
 
10,604,000 (85ኛ)
ገንዘብየሄይቲ ጓርዴ
ሰዓት ክልልUTC -5
የስልክ መግቢያ509
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ.ht

ሃይቲ በግብርና ፍሬያማ አገር ሆናለች፣ ለአለም የምታቀርባቸው ዋና ምርቶች በተለይ ቡናማንጎ፣ ካካው፣ ሙዝ ናቸው። የልብስ ፋብሪካ ኢንዱስትሪ ሰፊ ስለ ሆነ ካናቲራ፣ ሹራብ ወዘተ. ወደ ውጭ አገር ይላካል። እንዲሁም የማዕድን ኢንዱስትሪ በተለይ መዳብወርቅ ትልቅ ነው። ሌሎችም ታናናሽ ኢንዱስትሪዎች አሉ።