አልጀብራ

አልጀብራ በሂሳብ ጥናት ውስጥ ስለ ኦፕሬሽን፣ ዝምድናና ከነዚህ ሁለት ነገሮች ተነስተው ስለሚመጡት ፖሊኖሚያል፣ ተርም፣ የአልጀብራ አቋቋም የሚያጠና ነው። አልጀብራ የሚለው ስም የመጣው «አል ጃብር»፣ الجبر ከሚለው የአረብኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «መመለስ» ማለት ነው። ብዙው የአልጀብራ ዘዴ በአረብ ተማሪወች የተፈለስፈ ሲሆን ከነዚህ ቀደምት ተብሎ የሚጠራው መሃመድ ኢብን ሙሳ አል-ቋርዝሚ ነው።

ከአልቋርዝሚ መጽሃፍ አንድ ገጽ