ኮርንኛ

ይህ መጣጥፍ በብሪታንያ ስለሚገኘው ቋንቋ ነው። በእስያ ለሚገኘው ቋንቋ ለመረዳት፥ ኮሪይኛ ይመለከቱ።

ኮርንኛ (Kernowek) በእንግሊዝ የሚናገር ቋንቋ ነው። በኬልቲክ ቋንቋዎች ቤተሠብ ሆኖ የብረቶንኛና የዌልስኛ ቅርብ ዘመድ ነው።

የኮርንኛ ጠረፍ እስከ 1800 ዓ.ም. ድረስ ሲያንስ

የሚናገረው በእንግሊዝ አገር ደቡብ-ምዕራብ ጫፍ ወይም ኮርንዋል ነው። ቀደም ሲል ይህ ቋንቋ ከ1800 ዓ.ም. በፊት ጠፍቶ ነበር። በ20ኛው ክፍለ ዘመን ግን ስለ ቋንቋው አዲስ ትኩረት ተገኝቶ አሁን እንደ መነጋገርያ ታድሷልና 3,500 የሚያሕሉ ሰዎች ይችሉታል።

በ569 ዓ.ም. ከዴዮርሃም ውግያ ቀጥሎ የደቡብ-ምሥራቅ ብሪታንያ ሕዝቦች በዌልስ ከኖሩት ዘመዶቻቸው በሴያህስ ጀርመናዊ ወገን ተለያዩ። እንግሊዞች መንግሥታቸውን ሲያስፋፉም ብሪታኖች ያሠለጠኑት ግዛት በየጊዜው ይቀነስ ነበር። የኮርንዋል መንግሥት መጨረሻ በ922 ዓ.ም. እንግሊዞች ድል ሲያደርጋቸው ሆነ። ሆኖም ቋንቋቸው ከዚህ በኋላ ይፈራ ጀመር። ዛሬ ሶስት የአጻጻፍ ዘዴዎች አሉት።

ምሳሌ

አጠራርኮርንኛ (ይፋዊ አጻጻፍ)አማርኛ
ከርነወክKernowekኮርንኛ
ግወነነንgwenenenንብ
ካዶርcadorወንበር
ከውስkeusአይብ
ኢን-መስen-mesመውጫ
ኮድሃcodhaመውደቅ
ጋቨርgaverፍየል
chiቤት
ግወውስgweusከንፈር
አበርaberአፍ (የወንዝ)
ኒቨርniverቁጠር
ስኮልscolትምህርት ቤት
መጊmegyማጨስ
ስተረንsterenኮከብ
ኸድሂውhedhywዛሬ
ህዊባናwhibanaመፏጨት
ኮርንኛአጠራርአማርኛ
Mettin daምትን ዳመልካም ጥዋት
Dedh daመልካም ቀን
Fatla genes?ፋትላ ገነስእንዴት ነህ?
En poynt da, meur ras'እን ፖኢንት ዳ, ሜር ራስደህና እግዜር ይመስገን
Pe eur ew hi?ፒ ኤር ይው ሂ?ስንት ሰዓት ነው?
Ple ma Resrudh, mar pleg?ፕሌ ማ ርዝሩ, ማር ፕለግርዝሩዝ የት አለ እባክህ?
Ma Resrudh ogas dhe Gambron, heb mar!ኢማ ርዝሩ ኦጋስ ጋምብሮን, ኸብ ማር!ርዝሩዝ ለካምቦርን ቅርብ ነውኮ


Wikipedia