ቦሊቪያ


ቦሊቪያደቡብ አሜሪካ የሚገኝ አገር ነው። ዋና ከተማላፓዝ ነው።

ኤስታዶ ፕሉሪናሲዮናል ዴ ቦሊቪያ
Estado Plurinacional de Bolivia

የቦሊቪያ ሰንደቅ ዓላማ የቦሊቪያ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
ብሔራዊ መዝሙር Himno Nacional de Bolivia
«የቦሊቪያ ብሔራዊ መዝሙር»

የቦሊቪያመገኛ
የቦሊቪያመገኛ
ዋና ከተማላፓዝ
ሱክሬ (በይፋ)
ብሔራዊ ቋንቋዎችእስፓንኛ
መንግሥት
ፕሬዝዳንት
ፕሬዚዳንታዊ ሪፐብሊክ
ኤቮ ሞራሌስ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
ውሀ (%)
 
1,098,581 (27ኛ)
1.29
የሕዝብ ብዛት
የ2015 እ.ኤ.አ. ግምት
 
11,410,651 (81ኛ)
ገንዘብቦሊቪያኖ
ሰዓት ክልልUTC −4
የስልክ መግቢያ591
ከፍተኛ ደረጃ ከባቢ.bo

11 ሚሊዮን ሕዝብ ያሉበትና ምንም የባሕር ጠረፍ የሌለው አገር ነው። በ2001 ዓም ስሙ በይፋ ከ«የቦሊቪያ ሪፐብሊክ» ወደ «የቦሊቪያ ብዙ-ብሔሮች ሪፐብሊክ» ተቀየረ። ስሙ «ቦሊቪያ» ከ1817 ዓም. ጀምሮ ስለአብዮታዊው አለቃ ሲሞን ቦሊቫር ክብር ደረሰ። ከ1974 ዓም ጀምሮ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ኖርዋል።

ቦሊቪያ ከፍተኛ አንዴስ ተራሮች ሰንሰለት አለው፤ ላፓዝም ከማናቸውም የአለም ዋና ከተሞች ይልቅ ከባሕር ደረጃ በላይ ከፍተኛነት አለው። በጫፎቹም አመዳይ ይታያል። በዝቅተኛ ሥፍራዎች በጣም የሞቀ በረሃ አለ። እጅግ ብዙ የተለያዩ አትክልትና እንስሳት በቦሊቪያ ይገኛሉ።

አብዛኞቹ ሕዝቦች ከኗሪ ብሔሮች እንደ ቀቿና አይማራ ናቸው፤ ቋንቋዎቻቸው ሁሉ ከእስፓንኛ ጋራ መደበኛ የስራ ቋንቋዎች ሁኔታ አላቸው።

ልዩ ልዩ የጨፈራና የዘፈን አይነቶች አሉ። አበሳሰሉ በተለይ ባቄላበቆሎድንች ይጠቀማል። እግር ኳስ በተለይ የተወደደው እስፖርት ነው።