ውሻ

ውሻ Canis lupus familiaris በሚባለው ሳይንሳዊ ስም የሚታወቅ ከተኩላ የተላመደ የCanidae ቤተሰብ አባል ነው። የሠው ልጅ ከረጅም አመታት በፊት ቅድሚያ ካለመዳቸው እንስሳት መካከል ይጠቀሳል።

ውሻ

የውሻ አስተኔ ውስጥ አንዳንድ ሌሎች ዝርዮች ደግሞ በስማቸው «ውሻ» ይባላሉ፣ እንጂ የለማዳው ውሻ ዝርያ አይደሉም። እነሱም፦

  • የአፍሪካ ኣውሬ ውሻ
  • የእስያ አውሬ ውሻ
  • አጭር ጆሮ ውሻ (ደቡብ አሜሪካ)
  • የጫካ ውሻ (ደቡብ አሜሪካ)
  • የራኩን ውሻ (ምሥራቅ እስያ)

እንዲሁም በዘራይጥ መደብ ውስጥ በስሜን አሜሪካ የሚገኝ አንድ የሽኮኮ ወገን «የሜዳ ውሻ» ይባላል፤ እሱ በውነት የውሻ አስተኔ አባል አይደለም።