የዓረብኛ አልፋቤት

የዓረብኛ አልፋቤት ወይም የዓረብኛ አብጃድ በተለይ አረብኛን ለመጻፍ የተደረጀው አልፋቤት (አብጃድ) ነው። 28 ፊደሎች ሲኖሩት ከቀኝ ወደ ግራ በተያያዘ ጽሕፈት ይጻፋል።

የተደረጀው በስሜን አረብ ከቀደመው ናባታውያን አልፋቤት በ400 ዓም አካባቢ ነበረ። ይህም ናባታውያን አልፋቤት በፈንታው በ200 ዓክልበ. ያህል በዮርዳኖስ ከአራማይስጥ አልፋቤት ደረሰ፤ የአራማይስጥም በ800 ዓክልበ. ግድም በሶርያ ከፊንቄ አልፋቤት ተነሣ።

ተራ «አብጃዲ» ቀደም-ተከተል
غظضذخثتشرقصفعسنملكيطحزوهـدجبا
28272625242322212019181716151413121110090807060504030201

ከአረብኛ በላይ የዓረብኛ ጽሕፈት ብዙ ሌሎችን ልሳናት ለመጻፍ በጥቅም ላይ ውሏል፤ በተለይም አሁን ኡርዱፋርስኛፐንጃብኛውግርኛ በአረብ ጽሕፈት ይጻፋሉ። ለነዚህም ሌሎች ቋንቋዎች ድምጾች ተጨማሪ ልዩ ፊደላት ተለሙ።