ጀርመናዊ ቋንቋዎች

ጀርመናዊ ቋንቋዎችሕንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሠብ ቅርንጫፍ ሲሆን፣ ሁላቸው ከቅድመ-ጀርማንኛ ደረሱ።

የጀርመናዊ ቋንቋዎችና ቀበሌኞች ኗሪ አገሮች

የጀርመናዊ ቋንቋዎች ፫ ክፍሎች ምዕራብ ጀርመናዊ፣ ስሜን ጀርመናዊ፣ እና ምሥራቅ ጀርመናዊ ሲሆኑ ከነዚህ አንዱ ምሥራቅ ጀርመናዊ አሁን ጠፍቶ አይገኝም።

ምዕራብ ጀርመናዊ ቋንቋዎች

ዋና ቋንቋዎቹ እንግሊዝኛሆላንድኛ፣ እና ጀርመንኛ ሲሆኑ፣ በነዚህ ውስጥ አያሌ ንዑስ ቀበሌኞች አሉ። ምዕራብ ጀርመናዊ ቋንቋዎች ይዩ።

ስሜን ጀርመናዊ ቋንቋዎች

እነዚህ ሁላቸው ከጥንታዊ ኖርስኛ ደረሱ። አሁን ዋናዎቹ ኖርዌይኛስዊድኛዳንኛአይስላንድኛፋሮኛ ናቸው።

ምሥራቅ ጀርመናዊ ቋንቋዎች

እነዚህ ቋንቋዎች አሁን አይገኙም። ጎትኛ፣ የክሪሜያ ጎትኛ፣ ቫንዳልኛ፣ እና ቡርጉንድኛ ምሥራቅ ጀርመናዊ ልሳናት ነበሩ።