የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ

የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ፳ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሲሆን ከሰኔ ፭ እስከ ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፪ ዓ.ም. በብራዚል ይካሄዳል።[1] ብራዚል ይህን ውድድር ስታዘጋጅ ይሄ ሁለተኛ ጊዜዋ ነው። ፊፋ የ2014 እ.ኤ.አ. ውድድር በደቡብ አሜሪካ እንደሚካሄድ በ2007 እ.ኤ.አ. ካወጀ በኋላ ብራዚል ያለማንም ተቀናቃኝ አዘጋጅ አገር ሆና ተመርጣለች።

የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ

ይፋዊ ምልክት
ይፋዊ ምልክት
ይፋዊ ምልክት
የውድድሩ ዝርዝር
አስተናጋጅ ብራዚል
ቀናትከሰኔ ፭ እስከ ሐምሌ ፮ ቀን
ቡድኖች፴፪ (ከ፭ ኮንፌዴሬሽኖች)
ቦታ(ዎች)፲፪ ስታዲየሞች (በ፲፪ ከተማዎች)
ደቡብ አፍሪካ 2010 እ.ኤ.አ. ሩሲያ 2018 እ.ኤ.አ.

የ፴፩ አገራት ብሔራዊ ቡድኖች ከጁን 2011 እ.ኤ.አ. ጀምሮ የተካሄዱ የማጣሪያ ውድድሮችን በማለፍ ከብራዚል ጋር በመጨረሻው ውድድር ላይ ለመሳተፍ በቅተዋል። በጠቅላላው ፷፬ ጨዋታዎች በ፲፪ ከተማዎች ውስጥ በሚገኙ አዲስ የተገነቡ ወይም የተሻሻሉ ስታዲየሞች ይከናወናሉ። በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የጎል ላይን ቴክኖሎጂ በጥቅም ላይ ውሏል።[2]

በ1930 እ.ኤ.አ. ከተካሄደው የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ጀምሮ ሁሉም የዓለም ዋንጫ ሻምፕዮን አገራት (ብራዚል፣ አርጀንቲና፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሣይ፣ ጀርመን[ማስታወሻ 1]፣ ኢጣልያ፣ እስፓንያ እና ኡራጓይ) በዚህ ውድድር ውስጥ ተሳታፊ ናቸው። ከዚህ በፊት በደቡብ አሜሪካ የተዘጋጁትን ዋንጫዎች እንዳለ የወሰዱት የደቡብ አሜሪካ ቡድኖች ናቸው።[3]

ተሳታፊ አገራት እና ዳኛዎች

ማጣሪያ

ከጁን 2011 እስከ ኖቬምበር 2013 እ.ኤ.አ. የተካሄዱትን የማጣሪያ ጨዋታዎች ያለፉት አገራት ከውድድሩ በፊት ከያዙት ደረጃ ጋር ተዘርዝረዋል። ከነዚህ ውስጥ ቦስኒያና ሄርጸጎቪና ብቻ ከዚህ በፊት በዓለም ዋንጫ አልተሳተፈችም።[4][ማስታወሻ 2]

ኤ.ኤፍ.ሲ.

ካፍ

ኦ.ኤፍ.ሲ.

  • የለም

ኮንካካፍ

ኮንሜቦል

ዩኤፋ

  ማጣሪያ ያለፉ አገራት
  ማጣሪያ የወደቁ አገራት
  በማጣሪያ ውስጥ ያልተሳተፉ አገራት
  የፊፋ አባል ያልሆነ አገር

የምድብ ድልድል ዕጣ አወጣጥ

፴፪ቱ ተሳታፊ አገራት በአራት በ፬ ቋቶች ተደራጅተዋል። በፊፋ የብቃት ደረጃ ላይ የሚገኙት ምርጥ ፯ ቡድኖች ብራዚል ጨምረው በዘር ቋት (seeded pot) ውስጥ ተመድበዋል።[5] ቀሪዎቹ ቡድኖች በተቻለ መጠን ከተለያዩ ኮንፌዴሬሽኖች እንዲወጣጡ (ማለትም በአንድ ምድብ ውስጥ የሚገኙ አገራት በመልከዓምድር የተራራቁ እንዲሆን) በማድረግ በሌሎቹ ፫ ቋቶች ተመድበዋል።[6][7] የመደብ ድልድል ሥነ ስርዓቱ ኅዳር ፳፯ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ብራዚል በሚገኘው ኮስታ ዶ ሳዊፒ ሪዞርት ተካሄዷል።[8]

ቡድኖች

ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ቡድኖች

እንድ 2010 እ.ኤ.አ. ውድድር እያንዳንዱ ቡድን ፳፫ ተጫዋቾች ሲኖሩት ከነዚህም ውስጥ ፫ቱ ግብ ጠባቂ መሆን አለባቸው። እያንዳንዱ ብሔራዊ የእግር ኳስ ማህበር የሚያሰልፋቸውን ፳፫ ተጫዋቾች ውድድሩ ከመጀመሩ ፲ ቀናት በፊት ማሳወቅ ነበረበት።[9]

ቡድኖቹ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ተጫዋች ካጋጠማቸው ከመጀመሪያ ግጥሚያቸው 24 ሰዓት በፊት ድረስ መለወጥ ይችላሉ።[9]

ዳኛዎች

የፊፋ ዳኛዎች ኮሚቴ በጥር ፮ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከ፵፫ አገራት የተውጣጡ ፳፭ የዳኛ ሦስትዮሾችን እና ፰ ረዳት ጥንዶችን (አራተኛና አምስተኛ ዳኛዎች) ለውድድሩ ሾሟል።[10][11]

የሽልማት ገንዘብ

ፊፋ ለውድድሩ ያቀረበው ጠቅላላ የሽልማት ገንዘብ $576 ሚሊዮን ነው። ይህም ከ2010 እ.ኤ.አ. ውድድር ሽልማት ገንዘብ የ፴፯ ከመቶ ዕድገት አለው።[12] ከዚህ ውስጥ $70 ሚሊዮን የሚሆነው ተጫዋቾቹ ለሚጫወቱበት ክለቦች ተጫዋቾቹ ለሚደርስባቸው ጉዳት መካካሻ እንዲሆን ተሰጥቷል። ከውድድሩ በፊት እያንዳንዱ ቡድን ለዝግጅት ወጪው $1.5 ሚሊዮን የተረከበ ሲሆን ቀሪው ገንዘብ እንደሚመለከተው ተከፋፍሏል፦

  • $8 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በምድብ ደረጃ የወደቀ ቡድን (፲፮ ቡድኖች)
  • $9 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በየ፲፮ ዙር የወደቀ ቡድን (፰ ቡድኖች)
  • $14 ሚሊዮን - ለያንዳንዱ በሩብ ፍፃሜ የወደቀ ቡድን (፬ ቡድኖች)
  • $20 ሚሊዮን - በአራተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን
  • $22 ሚሊዮን - በሶስተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን
  • $25 ሚሊዮን - በሁለተኛ ደረጃ ለጨረሰው ቡድን
  • $35 ሚሊዮን - ለአሸናፊው ቡድን

ከተማዎችና ስታዲየሞች

በአስራ ሁለት ከተማዎች የሚገኙ አስራ ሁለት ስታዲየሞች ለውድድሩ ተዘጋጅተዋል። ሰባቱ አዲስ የተገነቡ ሲሆን አምስቱ ደግሞ የተሻሻሉ ስታዲየሞች ናቸው።

ሪዮ ዴ ጃኔይሮብራዚሊያሳው ፓውሉፎርታሌዛ
ኤስታዲዮ ዶ ማራካናኤስታዲዮ ናሲዮናልአሬና ዴ ሳው ፓውሉኤስታዲዮ ካስቴላው

22°54′43.8″S 43°13′48.59″W / 22.912167°S 43.2301639°W / -22.912167; -43.2301639 (Estádio do Maracanã)

15°47′0.6″S 47°53′56.99″W / 15.7835°S 47.8991639°W / -15.7835; -47.8991639 (Estádio Nacional Mané Garrincha)

23°32′43.91″S 46°28′24.14″W / 23.5455306°S 46.4733722°W / -23.5455306; -46.4733722 (Arena de São Paulo)

3°48′26.16″S 38°31′20.93″W / 3.8072667°S 38.5224806°W / -3.8072667; -38.5224806 (Estádio Castelão)

ቤሎ ሆሪዞንቴ
ፎርታሌዛ
ፖርቶ አሌግሬ
ሳልቫዶር
ናታል
ኩይባ
ማናውስ
ሬሲፌ
ፖርቶ አሌግሬ
ኤስታዲዮ ሚኔረውኤስታዲዮ ቤራ ሪዮ

19°51′57″S 43°58′15″W / 19.86583°S 43.97083°W / -19.86583; -43.97083 (Estádio Mineirão)

30°3′56.21″S 51°14′9.91″W / 30.0656139°S 51.2360861°W / -30.0656139; -51.2360861 (Estádio Beira-Rio)

ሳልቫዶርሬሲፌ
አሬና ፎንቴ ኖቫአሬና ፔርናምቡኩ

12°58′43″S 38°30′15″W / 12.97861°S 38.50417°W / -12.97861; -38.50417 (Arena Fonte Nova)

8°2′24″S 35°0′29″W / 8.04°S 35.00806°W / -8.04; -35.00806 (Arena Pernambuco)

ኩይባማናውስናታልኩሪቺባ
አሬና ፓንታናልአሬና ዳ አማዞኒያአሬና ዳ ዱናስአሬና ዳ ባይሻዳ

15°36′11″S 56°7′14″W / 15.60306°S 56.12056°W / -15.60306; -56.12056 (Arena Pantanal)

3°4′59″S 60°1′41″W / 3.08306°S 60.02806°W / -3.08306; -60.02806 (Arena Amazônia)

5°49′44.18″S 35°12′49.91″W / 5.8289389°S 35.2138639°W / -5.8289389; -35.2138639 (Arena das Dunas)

25°26′54″S 49°16′37″W / 25.44833°S 49.27694°W / -25.44833; -49.27694 (Arena da Baixada)

መሰልጠኛ ሰፈሮች

እያንዳንዱ ቡድን የራሱ የሆነ የመሰልጠኛና መቆያ ሰፈር አለው። ፊፋ ፹፬ ዕጩ ከተማዎችን ካስታወቀ በኋላ[13] በጥር ፳፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. እያንዳንዱ የተሳታፊ ቡድኖች የመረጡትን ከተማ ይፋ አርጓል።[14]

ቡድንከተማክፍላገርቡድንከተማክፍላገር
 አልጄሪያሰሮካባሳው ፓውሉ  ግሪክ (አገር)አራካጁሰርጂፒ
 አርጀንቲናቬስፓስያኖሚናስ ጄራይስ  ሆንዱራስፖርቶ ፌሊዝሳው ፓውሉ
 አውስትራልያቪቶሪያኤስፒሪቶ ሳንቶ  ፋርስጓሩሎስሳው ፓውሉ
 ቤልጅግሞጂ ዳስ ክሩዜስሳው ፓውሉ  ኢጣልያማንጋራቺባሪዮ ዴ ጃኔይሮ
 ቦስኒያና ሄርጸጎቪናጓሩጃሳው ፓውሉ  ኮት ዲቯርአጓስ ዴ ሊንዶያሳው ፓውሉ
 ብራዚልቲሪሶፖሊስሪዮ ዴ ጃኔይሮ  ጃፓንኢቱሳው ፓውሉ
 ካሜሩንቪቶሪያኤስፒሪቶ ሳንቶ  ሜክሲኮሳንቶስሳው ፓውሉ
 ቺሌቤሎ ሆሪዞንቴሚናስ ጄራይስ  ኔዘርላንድስሪዮ ዴ ጃኔይሮሪዮ ዴ ጃኔይሮ
 ኮሎምቢያኮቲያሳው ፓውሉ  ናይጄሪያካምፒናስሳው ፓውሉ
 ኮስታ ሪካሳንቶስሳው ፓውሉ  ፖርቱጋልካምፒናስሳው ፓውሉ
 ክሮኤሽያማታ ዴ ሳው ጁዋውባኺያ  ሩሲያኢቱሳው ፓውሉ
 ኤኳዶርቪያማውሪዮ ግራንጄ ዶ ሱል  ደቡብ ኮሪያፎዝ ዶ ኢጓሱፓራና
 እንግሊዝሪዮ ዴ ጃኔይሮሪዮ ዴ ጃኔይሮ  እስፓንያኩሪቺባፓራና
 ፈረንሣይሪቤራው ፕሬቶሳው ፓውሉ  ስዊዘርላንድፖርቶ ሴጉሮባኺያ
 ጀርመንካምፖ ባኺያ፣ ሳንታ ክሩዝ ካብራሊያባኺያ  አሜሪካሳው ፓውሉሳው ፓውሉ
 ጋናማሴዮአላጎአስ  ኡራጓይሴቼ ላጎአስሚናስ ጄራይስ

የምድብ ደረጃ

ምድብ ኤ

ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤመለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤ

ምድብ ቢ

ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ቢመለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ቢ

ምድብ ሲ

ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ሲመለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ሲ

ምድብ ዲ

ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ዲመለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ዲ

ምድብ ኢ

ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኢመለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኢ

ምድብ ኤፍ

ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤፍመለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤፍ

ምድብ ጂ

ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ጂመለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ጂ

ምድብ ኤች

ዋና መጣጥፍ፦ የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤችመለጠፊያ:የ2014 እ.ኤ.አ. ፊፋ የዓለም ዋንጫ ምድብ ኤች

ማስታወሻ

ማመዛገቢያ