F
የላቲን አልፋቤት | ||||||
---|---|---|---|---|---|---|
A | B | C | D | E | F | |
G | H | I | J | K | L | M |
N | O | P | Q | R | S | T |
U | V | W | X | Y | Z | |
ተጨማሪ ምልክቶች፦ | ||||||
Þ... |
F / f በላቲን አልፋቤት ስድስተኛው ፊደል ነው።
ግብፅኛ ሐጅ | ቅድመ ሴማዊ ዋው | የፊንቄ ጽሕፈት ዋው | የግሪክ ጽሕፈት ዲጋማ | ኤትሩስካዊ F | ላቲን F | ||
---|---|---|---|---|---|---|---|
|
የ«F» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት «ዋው» እንደ ሆነ ይታስባል። በዚህ ጽሕፈት ፊደሉ የበትር ስዕል መስለ። ለዚህም ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ።
በፊንቄ ጽሕፈት የፊደሉ ድምጽ እንደ ተናባቢ («ው») ሲሆን በጥንታዊ ግሪክ አልፋቤት ግን ይህ ምልክት የአናባቢ ድምጽ «ኢው» (Υ, υ) ለማመልከት ተጠቀመ። ቅርጹ ትንሽ ተለውጦ ግን ተነባቢውን «ው» ለማመልከት Ϝ ϝ («ዋው» ወይም «ዲጋማ») ተጠቀመ። ከዚህ በኋላ «ው» የሚለው ተነባቢ ከግሪክኛ አነጋገር ስለ ጠፋ፣ «Ϝ ϝ» ለቁጥር (፮) ብቻ ሆነ። (ደግሞ ስቲግማ ይዩ።)
በኤትሩስክኛ ደግሞ «F» ለተነባቢው «ው» ይወክል ነበር። የ«ፍ» ድምጽ ለመወክል «FH» ተጻፈ። በሮማይስጥ ሌላ ምልክት «V» ለ«ው» ስለ ተጠቀመ፣ በላቲን ፊደል ፊደሉ «F» ለ«ፍ» ሊወክል ጀመር።
በግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ወ» («ዋዌ») የሚለው ፊደል ከቅድመ-ሴማዊው «ዋው» ስለ መጣ፣ የላቲን 'F' ዘመድ ሊባል ይችላል። እንዲሁም የላቲን U፣ V፣ W፣ እና Y ሁሉ ከ«ዋው» ደረሱ።
🔥 Top keywords: ዋናው ገጽውክፔዲያ ውይይት:ምንጭጌልዩ:Searchአበበ ቢቂላኃይሌ ገብረ ሥላሴየኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማእርዳታ:ይዞታኢትዮጵያጥሩነሽ ዲባባስዕል:Keristo1.pdfሥርዓተ ነጥቦችቪየናአማርኛፋይዳ መታወቂያምሥራቅ አፍሪካሥነ-ፍጥረትግብረ ስጋ ግንኙነትመዝገበ ቃላትየኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠርቅድስት አርሴማየአድዋ ጦርነትማርያምSpecial:Searchቅዱስ ያሬድአዲስ አበባ2ኛው ዓለማዊ ጦርነትአክሊሉ ለማ።ሽመናእስራኤልዓረፍተ-ነገርመሬትደራርቱ ቱሉመስተፃምርኣበራ ሞላውይይት:ዋናው ገጽእምስዐቢይ አህመድውክፔዲያቤተክርስቲያን